Your cart is currently empty!
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የመኪና ጎማ፣ ባትሪና ጌጣጌጥ ግዥ፣ የቢሮ አላቂ የፅህፈት መሣሪያ፣ ካሜራ፣ አምፒሊፋየርና ተዛማጅ ዕቃዎች፣ የህንፃ ጥገና እና ዕድሳት አገልግሎት እና የቢሮ መሬት ምንጣፍ እና መጋረጃ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 12, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን፡-
- በግልፅ ጨረታ ቁጥር ቤ/ል/ኮ/ግ/ጨ/003/2018
- በሎት-1 የመኪና ጎማ፣ ባትሪና ጌጣጌጥ ግዥ
- በሎት-2. የቢሮ አላቂ የፅህፈት መሣሪያ፣ ካሜራ፣ አምፒሊፋየርና ተዛማጅ ዕቃዎች፤
- በግልፅ ጨረታ ቁጥር ቤ/ል/ኮ/ግ/ጨ/004/2018 የህንፃ ጥገና እና ዕድሳት አገልግሎት፤
- በግልፅ ጨረታ ቁጥር ቤ/ል/ኮ/ግ/ጨ/005/2018 የቢሮ መሬት ምንጣፍ እና መጋረጃ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በዘርፉ የ2017/2018 የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ እና ንግድ ምዝገባ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ከሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ በድረ ገፅ /Online/ የተመዘገቡ መሆናቸውን ማስረጃቸውን ኮፒና ኦርጅናል አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ባንቢስ አካባቢ ግሪክ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት ያለው ህንፃ ላይ 4ኛ ፎቅ በኮርፖሬሽኑ የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን በግልፅ ጨረታ ቁጥር ቤ/ል/ኮ/ግ/ጨ/003/2018 ለሎት-1፣ ለሎት-2 እንዲሁም ለግልፅ ጨረታ ቁጥር ቤ/ል/ኮ/ግ/ጨ/005/2018 የቢሮ መሬት ምንጣፍ እና መጋረጃ ለእያንዳንዳቸው ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) እንዲሁም ለግልፅ ጨረታ ቁጥር ቤ/ል/ኮ/ ግ/ጨ/004/2018 ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይንም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው የሚከፈተው፡-
- የመሬት ምንጣፍ እና መጋረጃ ጥቅምት 14 ቀን 2018 ዓ.ም
- የመኪና ጎማ ባትሪና ጌጣጌጥ ግዥ ጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ.ም
- የቢሮ አላቂ የፅህፈት ዕቃዎች ግዥ ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም
- የህንፃ ጥገና እና ዕድሳት አገልግሎት ጥቅምት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ተወካዮች በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የመንግስት ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ 9ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 901 ይከፈታል።
ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01
ባንቢስ አካባቢ ግሪክ ት/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው የቤቶች ልማት ሕንፃ
ስልክ ቁጥር፡- 09 36 99 35 20/ 09 11 36 97 83
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን