Your cart is currently empty!
በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቃሉ ወረዳ ፍርድ ቤት የፅህፈት መሳሪያ፣ ደንብ ልብስ፣ ህትመት፣ የፅዳት እቃ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቋሚ የቢሮ እቃ፣ መስተንግዶ እና HIV ሚኒስትሪሚንግ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 14, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር -ግ/ፋ/ን/አስ/ 361 2018
የቃሉ ወረዳ ፍ/ቤት አገልግሎት የሚውል
- ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያ፣
- ሎት 2 ደንብ ልብስ፣
- ሎት 3 ህትመት፣
- ሎት4 የፅዳት እቃ፣
- ሎት 5 ኤሌክትሮኒክስ፣
- ሎት 6 ቋሚ የቢሮ እቃ፣
- ሎት 7 መስተንግዶ እና HIV ሚኒስትሪሚንግ ለ2018 በጀት አመት በአዲስ ዘመን ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች በተዘረዘረው መስፈርት መሰረት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
በዚህም መሰረት፡-
- ተጫራቾች ሕጋዊ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ቲንነበር ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና መረጃ ኦርጅናልና የማይመለስ ኮፒ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ መታሸግ አለባቸው።
- በተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ የሚያቀርቡት ዋጋ ከነቫቱ ነው።
- ማንኛውም ተወዳዳሪ የሚሞሉት ዋጋ ከ200 ሺህ ብር እና በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የእያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ ለየብቻው በማንኛውም ፖስታ በማሸግ ኦርጅናልና ኮፒዎችን በመለየት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ግልፅ ጨረታ ከወጣበት ከ 04/02/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 28/02/2018 ዓ.ም 11፡30 ሰዓት ድረስ ቃሉ ወረዳ ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 በመምጣት የተዘጋጀውን የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በጥሬ ገንዘብ በመክፈል ሰነድ መግዛት ትችላላችሁ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸው ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የቃሉ ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/ አስ/ ቢሮ ቁጥር 14 በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 29/02/2018 ዓ/ም በማስገባት በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ከተጠቀሰው ቀንና ሰአት ዘግይቶ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተነገራቸው በኋላ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ ራስን ማግለል አይቻልም።
- የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የበአል ቀን ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰአት የሚከፈት ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2% ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቃሉ ወረዳ ፍ/ቤት የተቆረጠ ህጋዊ ደረሠኝ ማስያዝ የሚገባችሁ ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ የምታቀርቡ ከሆነ የቆይታ ጊዜው 60 ቀንና ከዚያ በላይ መሆን መቻል ይኖርበታል።
- የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት በኋላ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ውስጥ የዋጋውን የውል ማስከበሪያ 10% ሲፒኦ በማስያዝ ውል መውሰድ ይኖርባቸዋል፣
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን እቃዎች በአሸነፈበት ዋጋ በፍትህ ጽ/ቤት ቀርቦ ውል ለመውስድ ፈቃደኛ የሆነ መሆን አለበት።
- ሁሉም የጨረታ ስነድ ላይ ፊርማ መኖር የሚገባው ሲሆን ስርዝ ድልዝ ቢያጋጥም በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል።
- መ/ቤቱ ከአሸናፊው ድርጅት ወይም ግለሰብ ከአሸነፈው ዕቃ ወይም ገንዘብ ላይ 30% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች የአማራ ክልል ገ/ኢ/ት/ቢሮ ያወጣውን የግዥ አፈጻጸም መመሪያ አዋጅ ቁጥር 1/2003 እና ተሻሽለው ለወጡ መመሪያዎችና አዋጆች ተገዥ መሆን አለባቸው።
- አሸናፊው ድርጅት በቃሉ ወረዳ ፍ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆነ መሆን አለበት።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ውድድሩ በእያንዳንዱ ሎት ድምር ሆኖ ሳለ ፍ/ቤቱ የመንግስትን ጥቅም የሚያስከብር ሆኖ ካገኘው በተናጠልም የምናወዳድር መሆኑን መታወቅ አለበት።
- አሸናፊው ተወዳዳሪ የሚያቀርበው ዕቃ ጥራቱን የጠበቀ (ኦሪጅናል) ዕቃዎችን የማቅረብ ግዴታ አለበት።
- ለተጨማሪ መረጃ በቃሉ ወረዳ ፍ/ቤት በስ/ቁ 033-551-29-61 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት የቃሉ ወረዳ ፍ/ቤት
cttx Advertising and Promotion cttx, cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Computer and Accessories cttx, cttx Consultancy cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Furniture and Furnishing cttx, cttx Health Care, cttx Health Related cttx, cttx Health Related Services and Materials cttx, cttx House Furniture cttx, cttx IT and Telecom cttx, cttx Office Furniture cttx, cttx Office Machines and Accessories cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Printed Advertising Materials cttx, cttx Printing and Publishing cttx, cttx Promotional Items cttx, cttx Public Address Systems cttx, cttx Shoes and Other Leather Products cttx, cttx Stationery cttx, cttx Textile, Electromechanical and Electronics cttx, Garment and Leather cttx, Garments and Uniforms cttx, Medical Industry cttx