Your cart is currently empty!
በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የምርጥ አቅርቦት ዘርፍ በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ላይ የሚገኘውን የተለያየ ዓይነት ያላቸው ፖሊ ባግ (Poly Bags) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 15, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የተለያዬ ዓይነት ያላቸው ፖሊ ባግ (Poly Bags) ሽያጭ
የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢግስኮ – ምዘአዘ/ጨሽ/ 01 ሠነድ/2018
በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የምርጥ አቅርቦት ዘርፍ በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ላይ የሚገኘውን የተለያዬ ዓይነት ያላቸው ፖሊ ባግ (Poly Bags) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ስለሚፈልግ፡–
1. ማንኛውም ተጫራች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላችሁ እና የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈሉ፡፡
2. ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ ስም የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በባንክ በተረጋገጠ በCPO ዋስትና ማስያዝ አለበት፡፡
3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ሰዓት (11፡00 ሰዓት በፊት) በዘርፍ ጽ/ቤት ቃሊቲ ጉምሩክ ፊት ለፊት አዲስ አበባ ዋናው መ/ቤት ወይም በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
4. ማንኛው ተጫራች የተገለፀውን መጠን የተለያዬ ዓይነት ያላቸው ፖሊ ባግ (Poly Bags) መጫረት ይችላል፡፡
5. ማንኛውም ተጫራች የተለያዬ ዓይነት ያላቸው ፖሊ ባግ (Poly Bags) በሚገኙበት ቅ/ጽ/ቤቶች በመገኘት አይቶ መጫረት አለበት፡፡ ይህን ሳያደርግ ዋጋ ቢያቀርብ ኃላፊነቱ የተጫራቹ ይሆናል፡፡
6. ማንኛውም ተጫራች የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የሚጠይቀውን በሙሉ አሟልቶ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
7. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
8. የተለያዬ ዓይነት ያላቸው ፖሊ ባግ (Poly Bags ) መጠን በዚህ ጨረታ ሠነድ ላይ ከተገለፀው መጠን ሊያንስ ይችላል፡፡
9. ዋጋውን በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማስገባት የሚቻል ሲሆን ጨረታው ጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ በ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዘርፍ ጽ/ቤት አዳራሽ እና በቅ/ጽ/ቤቶች ጨረታው ይከፈታል፡፡
10. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 011 618 6125
አዲስ አበባ
በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ