Your cart is currently empty!
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ቱሪዝም ኮሚሽን የገልማ አባ ገዳ ማዕከል ለካፍቴሪያ አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ መፈጸም ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 16, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ቱሪዝም ኮሚሽን የገልማ አባ ገዳ ማዕከል ለካፍቴሪያ አገልግሎት የሚውሉ ከታች በተዘረዘረው መሰረት በንግድ ዘርፉ የተሰማሩ ሕጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ መፈጸም ስለሚፈልግ ተፈላጊውን መስፈርት የምታሟሉ ድርጅቶችን /ግለሰቦችን/ ለ1 ዓመት ውል በመግባት ግዥ መፈጸም / መግዛት/ ስለሚፈልግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።
የዕቃዎቹ ዝርዝር፡–
- ሎት 1 – የምግብ ግብዓቶች፣ አትክልትና ፍራፍሬ፤
- ሎት 2 – ወተትና የወተት ተዋጽኦ ወዘተ፤
- ሎት 3 – ሌሎች የምግብ እህሎች /የእንጀራ ሩዝ፣ ገብስ፣ የዳቦ/ስንዴ ዱቄት እና ሌሎች የፋብሪካ ምርቶች፤
- ሎት 4 – የዶሮ ስጋ፣ የዓሳ ስጋ፣ እንቁላል፣
- ሎት 5 – የማገዶ እንጨት፣
- ሎት 6 – የቁም የእርድ ከብት (ለስጋ የሚሆን)፤
በዚሁ መሰረት፡–
1. ተጫራቾች በጨረታ ለመካፈል ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የሚፈለግባቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉ አጠናቀው ስለመክፈላቸው በቂ ማስረጃ (ክሊራንስ) ማቅረብ የሚችሉ፤ የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚሁ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል። እንዲሁም የንግድ መለያ ቁጥር (TIN) እና በእቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የምስከር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት (15) ተከታታይ ቀናት በኦሮሚያ ከልላዊ መንግስት ቱሪዝም ኮሚሽን የገልማ አባ ገዳ ማዕከል ጽ/ቤት ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 110 የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
4. የጨረታ ሠነዱ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስራ አምስተኛው (15) ኛው ተከታታይ ቀናት ይሸጥና በአስራ ስድስተኛው (16) ኛው የስራ ቀን በ3፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት በ3፡30 ሰዓት ይከፈታል።
5. አሸናፊው ድርጅት ለውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ላይ አስር ከመቶ (10/100) በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ አለበት።
6. የውል ማስከበሪያውም አሸናፊው ድርጅት ዕቃዎቹን በውሉ የጊዜ ገደብ አስገብቶ እስኪያጠናቅቅ ድረስ ተይዞ የሚቆይ ይሆናል።
7. ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸውን የምግብ ግብዓቶች ለማቅረብ ለ1 ዓመት ውል መፈረም ይጠበቅባቸዋል።
8. ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸውን እቃዎች በራሳቸው የትራንስፖርት ወጪ ጭነው አዳማ ገልማ አባ ገዳ ማዕከል ጽ/ቤት ድረስ በማቅረብ ማስረከብ ይኖርባቸዋል።
9. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን በተናጠል በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የድርጅቱ ማህተም አርፎበት መ/ቤቱ ለዚሁ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በጨረታው የመክፈቻ እለት ማስገባት አለባቸው።
10. ሌሎች ዝርዝር ማብራሪያዎች ከሚሸጠዉ የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ።
11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር፡– 022-1-12-45-65 / 022-2-12-92-55 ደውለው አስፈላጊ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ቱሪዝም ኮሚሽን የገልማ አባ ገዳ ማዕከል