Your cart is currently empty!
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. አክስዮኖች እና B+G+5 የንግድ ሕንፃ ንብረቶች በግልፅ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 16, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የሐራጅ ማስታወቂያ
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አማ በአዋጅ ቁጥር 97/1990 እና 216/1992 እንዲሁም በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 በተሰጠው ስዕጣን መሰረት በሰንጠረዡ ላይ የተዘረዘሩትን ንብረቶች በግልፅ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም |
የንብረት አስያዥ ስም |
አበዳሪ ቅርንጫፍ |
የንብረቱ አድራሻ |
የቦታው ስፋት (ሜ2) |
የባለቤትነት ማረገጫ ምስክር ወረቀት |
የንብረቱ አይነት |
የጨረታ መነሻ ዋጋ |
ጨረታው የሚከናወንበት ሰዓት |
|||
|
ከተማ |
ክ/ከተማ |
ወረዳ |
ቤ.ቁ |
|||||||||
|
1 |
ሚዛን ገብረ ፃዲቅ |
ሚዛን ገብረ ፃዲቅ |
የካ
|
ሽሬ እ/ስላሴ
|
— |
— |
— |
428.85 |
1729,4366/2013 |
B+G+5 የንግድ ሕንፃ
|
90,775,125.44
|
ጨረታው የሚከናወነው በባንኩ ሽሬ እ/ስላሴ ቅርንጫፍ ሕዳር 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ድረስ ይሆናል፡፡ |
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም |
የንብረት አስያዥ ስም |
አበዳሪ ቅርንጫፍ
|
የአክስዮኑ ዓይነት፤ መለያ ቁጥር፣ ብዛት እና የአክስዮን ዋጋ |
የጨረታ መነሻ ዋጋ
|
ጨረታው የሚከናወንበት ቀን እና ሰዓት |
|||
|
አክስዮኖቹ የሚገኙበት ድርጅት
|
የአክስዮኖቹ ምስክር ወረቀት ቁጥር |
የአክስዮኖቹ ብዛት
|
የአንዱ አክስዮኖቹ ዋጋ /በብር/ |
||||||
|
2 |
ዲ.ኤ.ቲ አስመጪና ላኪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር |
አቶ ተክለብርሃን ገብረክርስቶስ ገ/ገርግስ
|
ሻላ
|
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ |
21970
|
2500
|
1000
|
2,500,000 |
ጨረታው ሚከናወነው በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ጥቅምት 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ድረስ ይሆናል። |
ማሳሰቢያ፡–
- ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4ኛ) ወይም 25% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (CPO) ብቻ በአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አማ ስም በማሰራትና ለጨረታ ማስከበሪያነት በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
- ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ በተመለከተ በተ.ቁ 1 ላይ የተጠቀሰው ንብረት ጨረታ የሚካሄደው ንብረቱ በሚገኝበት ከተማ ባለው የባንኩ ቅርንጫፍ ይሆናል፡፡ በተ.ቁ 2 ላይ የተጠቀሰው ንብረት በተመለከተ ጨረታ የሚካሄደው 22 አካባቢ በሚገኘው ሌክስ ፕላዛ ሕንፃ ላይ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት የስብሰባ አዳራሽ ይሆናል።
- የተጫራቾች ምዝገባ የሚከናወነው በጠዋቱ ክፍለጊዜ 4፡00 – 5:30 ድረስ ይሆናል። ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኋላ ለንብረቱ የሚመደበው የጥሪ ሰዓት 30 ደቂቃ ብቻ ሲሆን የጨረታው መጠናቀቂያ ሰዓት ድረስ አሸናፊው ካልተለየ አሸናፊ እስኪለይ ድረስ ጨረታው የሚቀጥል ይሆናል።
- በጨረታው የተሻለ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ጨረታውን ከሚያካሂደው የባንኩ የህግ አገልግሎት መምሪያ ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ሲደርሰው ብቻ አሸናፊ ይባላል።
- የጨረታው አሸናፊ ቀሪውን ገንዘብ አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በአስራ አምስት (15) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ የሐራጁ ውጤት ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ (CPO) ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ይመለስላቸዋል።
- የጨረታው አሸናፊ ካሸነፈበት ዋጋ ላይ 15% (አስራ አምስት በመቶ) ተጨማሪ እሴት ታክስ ጨምሮ ይከፍላል።
- ለጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች ለመጎብኘት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጨረታው ቀን ከመድረሱ ከ7 (ሰባት) የስራ ቀናት አስቀድሞ ከባንኩ ጋር ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይችላል።
- በሐራጅ ጨረታው ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪዎች እና ንብረት አስያዥ ወይም የነዚህ ሕጋዊ ተወካዮች ብቻ ናቸው። ተበዳሪዎች እና ንብረት አስያዦች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታውን ሂደት ለመከታተል በተጠቀሰው ቦታ እና ሰዓት እንድትገኙ እያሳሰብን ካልተገኛችሁ በሌላችሁበት ጨረታው የሚከናወን መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ባንካችን ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይፅፋል።
- ከሚሸጠው ንብረት ጋር የተያያዙ ከጨረታው በፊትም ሆነ በኋላ ማንኛውም ለመንግስት ሊከፈሉ የሚገባቸው የሊዝ ክፍያዎች፣ ወጪዎች ወይም ግብር እንዲሁም በንብረት ማስተላለፍ ሂደት የሚመጡ ማንኛውም አይነት ክፍያዎች ወይም ግብር ሙሉ በሙሉ የጨረታ አሸናፊው ገዥው የሚሸፍን ይሆናል።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ ማብራርያ ወይም የጉብኝት ቀጠሮ ለማመቻቸት አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. ዋና መ/ቤት ሕግ አገልግሎት መምሪያ በስልክ ቁጥር 011-662-7120 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ.