በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የደቡብ ወሎ መስተዳድር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 17, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር፡ደወ/ከፍ/001/2018

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የደቡብ ወሎ መስተዳድር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለመስሪያ ቤቱ እንዲሁም ለአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደሴ ቋሚ ምድብ ችሎት ስራ ማስፈጸሚያ አገልግሎት የሚዉሉ ቀጥለዉ የተዘረዘሩትን እቃዎችና አገልግሎቶች ማለትም በህንጻው ላይ የሚገኘውን ካፍቴሪያ ለዳኞች፣ዐ/ህጎች እና ሰራኞች በተጨማሪም ለውጭ ተገልጋዮች አገልግሎት የሚውል ትኩስ መጠጦች፣ ምግብ እና ውሃና ለስላሳ መጠጦችን እንዲሁም የፎቶ ኮፒ አገልግሎት የፍትሐብሄር፣ ወንጀል፣ የደሴ ቋሚ ምድብ ችሎት እና ሰበር ሰሚ ችሎቶች ኮፒ እየተደረጉ ለሚመለከተው አካል የሚተላለፍ መዛግብቶችን ኮፒ ማደረግና ለነዚህ ሁለቱ አገልግሎት ግዥዎች የቤት ኪራይ፣ የመብራት እና ውሃ ወጪዎችን መ/ቤቱ ይሸፍናል። በዚህ መሰረት መ/ቤቱ እነዚህን ከታች የተዘረዘሩትን የጨረታ ሎቶች ለማጫረት ይፈልጋል፡- ማለትም

  • 1ኛ. የጽህፈት መሳሪያዎችን የቢሮ አላቂ እቃዎችን፤
  • 2ኛ. ቋሚ አላቂ ዕቃዎችን /ልዩ ልዩ መሳሪያዎችን
  • 3ኛ. የጽዳት እቃዎችን /ሌሎች አላቂ እቃዎችን/፤
  • 4ኛ. የህትመት ስራዎችን፤
  • 5ኛ. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን፤
  • 6ኛ. ልዩ ልዩ ቋሚ የቢሮ መገልገያ መሳሪያዎችን ፈርኒቸርና ሌሎችም
  • 7ኛ. የመኪና እቃ መለዋወጫ፤
  • 8ኛ. የመኪና ጎማና ባትሪ፤
  • 9ኛ. የደንብ ልብስና ተዛማጅ እቃዎችን፤
  • 10ኛ. የፎቶ ኮፒ አገልግሎት /አወት ሶርስ/፤
  • 11ኛ የካፌ አገልግሎት፤
  • 12ኛ. የመኪና ዘይቶች፤

በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

 ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር የሚችሉ መሆኑን መ/ቤቱ ይጋብዛል።

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው፤
  4. የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ / VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  6. የሚገዙ የእቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶችን ማለትም ከተ.ቁ 1-9 የተዘረዘሩትን የጨረታ ሰነዶች ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 70.00 /ሰባ ብር/ በተ.ቁ 10 -12 ላይ የተዘረዘሩትን የጨረታ ሰነዶች ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 50.00 /ሀምሳ ብር/ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ደ/ወ ከፍ/ፍ/ቤት ግዥና ፋይ/ን/አስ/ቢሮ ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ ለካፌ አገልግሎት 5000 አምስት ሺህ ብር እንዲሁም ለፎቶ ኮፒ አገልግሎት 8000 ስምንት ሺህ ብር ቫትን ጨምሮ ሌሎች ግን %1 በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ ደረቅ ቼክ ማስያዝ አይቻልም።
  9. አንድ ተጫራች በአንድ ሎት ውስጥ ከተዘረዘሩት የዕቃ አይነቶች መካከል ከፋፍሎ መረት አይቻልም። ሆኖም በሎቱ ውስጥ ከተዘረዘሩት ዕቃዎች ውስጥ አንድ ዕቃ ዋጋ ሳይሰጥበት ቢቀር ተጫራቹ ድርጅት ከጨረታ ውጭ የሚሆን ይሆናል።
  10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን ሰነዱን አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት እስከ 16ኛው ቀን 4:00 ሰዓት ድረስ ደ/ወ/ዞ/ከ/ፍ/ቤት ግዥ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 501 በመገኘት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቢሮ በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ላይ በይፋ ይከፈታል። የመክፈቻው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ላይ በይፋ ይከፈታል።
  12. መ/ቤቱ ጨረታውን የሚያወዳድረው በሎት ነው።
  13. መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  14. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ መ/ቤቱ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋከስ ቁጥር 033-1-11-44-28 ወይም በስልክ ቁጥር 033-1-11-82-21 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት