Your cart is currently empty!
በሀዲያ ዞን የሆሳዕና ከተማ አስ/ር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 በፊደል ተራ ከሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሠረት ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች (ለመኖሪያ እና ለንግድ) የተዘጋጀ ቦታን በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 17, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታው ዙር፡– 1ኛ
1. የጨረታ ዓይነት ፡ መደበኛ
2. በሀዲያ ዞን የሆሳዕና ከተማ አስ/ር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 በፊደል ተራ ከሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሠረት ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች (ለመኖሪያ እና ለንግድ) የተዘጋጀ ቦታን በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 300 ብር በመክፈል ከማዘጋጃ ቤቱ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ዘርፍ ቢሮ ቁጥር 3 እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ብቻ መግዛት የሚቻል መሆኑን እናስታውቃለን፡፡ ለመደበኛ ጨረታ በ10ኛው ቀን የጨረታ ሰነድ የሚሸጠው እስከ 9፡00 ሰዓት ብቻ ነው።
3. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/ አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ብቻ ይሆናል።
4. የጨረታው ሳጥን የሚታሸገው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣበት 10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ይሆናል።
5. ቦታውን መጎብኘት ለሚፈልግ ተጫራች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገለጸው መርሐ ግብር መሠረት የምናስጎበኝ ይሆናል።
6. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣበት በ11ኛው ቀን ከቀኑ 4፡30 ሰዓት በሆሳዕና ከተማ አቢዮ ኤርሳሞ ስታዲየም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡ 11ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።
7. ስለ ጨረታው ዝርዝር ማብራሪያ ከጨረታው ሰነድ ማግኘት ይቻላል።
8. ማዘጋጃ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
9. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ዌብ ሳይት www.hosannaca.gov.et ማግኘት ይቻላል
ለተጨማሪ መረጃ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች ደውሎ ማግኘት ይቻላል።
046-555-3645
046-555-2355
046-555-2310
የሆሳዕና ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገ/ቶች ጽ/ቤት /ሆሳዕና/