Your cart is currently empty!
አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ አንደኛ ደረጃ ልዩ ፍላጎት ት/ቤት በ2018 አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 18, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የጨረታ ማስታወቂያ
አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ አንደኛ ደረጃ ልዩ ፍላጎት ት/ቤት በ2018 አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ እቃዎች
- የደንብ ልብስ
- አላቂ የቢሮ እቃዎች
- አላቂ የትምህርት እቃዎች
- አላቂ የጽዳት እቃዎች
- ልዩ ልዩ መሳሪያዎች እቃዎች
- ቋሚ እቃዎች
በዚህ መሠረት
ሎት1. 8,000 ሎት2 2,000 ሎት3. 6,000 ሎት4 12,000 ሎት5 2,000 ሎት 6 20,000
በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል በዚህ መሰረት ተጫራቾች ሊያሟሉ የሚገባቸው
1.በመንግስት እቃ አቅራቢነት ተመዝግበው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና ቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2.ተጫራቾች የአንዱን ዋጋ ሲያቀርቡ ቫትን ደምረው ማቅረብ አለባቸው ተጫራቾች በዘርፉ ወይም በመስኩ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው።
3.የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ተጨማሪ ክሊራንስ ከገቢዎች ማቅረብ የሚችል።
4.ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
5.ተጫራቾቹ ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ባለው ፋይናንስ ክፍል በመገኘት ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይቻላል።
6.ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ በገዙበት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልፅ በመሙላት በመጨረሻም ቦታ ላይ ስም ፊርማ እና ህጋዊ ማህተም በማኖር በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት 2፡30- 11፡30 ዋጋቸውን በመሙላት በተጠቀሰው የስራ ሰዓት የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል።
7.ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች እና በፎቶ የሚቀርቡትን ጨረታው ሊዘጋ አንድ ቀን እስኪቀረው ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
8.ጨረታውን አሸናፊ ሆነው ከተገኙ 10% ባሸነፉበት እቃ መጠን መሰረት የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባችኋል።
9.ጨረታውን ለማባዛት የሚሞክር ከጨረታው ውጭ እንደሚሆን የጨረታው ማስከበሪያ ሲፒኦ እንደሚውስድባቸው ማወቅ አለባቸው።
10. ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስራ አንደኛው ቀን ልክ 4፡30 ላይ ይከፈታል።
11.ማንኛውም ተጫራች የገዛውን ሰነድ የሚሞላውን በመሙላት በእያንዳንዱ ገፅ ላይ ማህተም በማድረግ ሳይጨምር ሳይቀንስ መመለስ ይኖርበታል።
12.የጨረታ ውል ማስከበሪያ ሲፒኦ 10%ፐርሰንት ማስያዝ አለበት።
13.ለጥቃቅን እና አነስተኛ ተጫራቾች የሀገር ውስጥ ምርት ላይ የተሣተፉ መሆናቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ከሚመለከታቸው ህጋዊ አካል ካላመጡ የሰነድ ማስከበሪያ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ለእያንዳንዱ ሎት ማስያዝ አለባቸው።
14.የግዥ ፈጻሚው አካል ተጫራቾች በሚጠሩበት ጊዜ የገዛውን እቃ መጠን እንደ አስፈላጊነቱ እስከ (20%) ሃያ ለመቀነስ ወይም መጨመር ይችላል።
አድራሻ፡- አቃ/ቃ/ክ/ከ ወረዳ 12 ገላን ኮንዶምኒየም ታክሲ ተራ ወረድ ብሎ ሮቢክ ፊት ለፊት አስፋልቱን ተሻግሮ ገላን መስኪጊድ ወረድ ብሎ፡፡
አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ አንደኛ ደረጃ ልዩ ፍላጎት ት/ቤት