Your cart is currently empty!
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የእነዋሪ ቴ/ሙ/ማ ኮሌጅ የግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን በ2018 በጀት አመት በኮሌጁ ውስጥ ለአገልግሎት የሚውሉ የፅህፈት መሳሪያ፣ የቢሮ መገልገያ እቃዎች ህንፃ፣ ፕላንት ማሽነሪ፣ የፅዳት እቃዎች፣ አላቂ የትምህርት እቃዎች እና የህንፃ መገልገያ መሳሪያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 18, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የእነዋሪ ቴ/ሙ/ማ ኮሌጅ የግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን በ2018 በጀት አመት በኮሌጁ ውስጥ ለአገልግሎት የሚውሉ
- ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያ፣
- ሎት 2 የቢሮ መገልገያ እቃዎች ህንፃ፣
- ሎት 3 ፕላንት ማሽነሪ፣
- ሎት4 የፅዳት እቃዎች
- ሎት 5 አላቂ የትምህርት እቃዎች
- ሎት6 የህንፃ መገልገያ መሳሪያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ እና በየንግድ ዘርፉ የተሰማሩ ሆነው መጫረት የሚፈልጉ የንግድ ድርጅቶች
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)ያላቸው
- የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ያለው
- የገዥው መጠን ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር እና ከዚያ በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የእቃውን አይነት ዝርዝር መግለጫ ወይም እስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር ብቻ በመከፈል ከእነዋሪ ቴ/ሙ/ማ ኮሌጅ የፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 005 የሰነድ ክፍያ በመፈፀም የጥሬ ገንዘብ ገቢ ደረሰኝ በመያዝ ከግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 003 ሰነዱን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- ተጫራቾች ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 3% የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ገቢ ደረሰኝ ወይም ከታወቁ ባንኮች የሚሰጥ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚሰጡትን የጨረታ ዋጋ የጨረታ ሰነዱ በሚጠይቀው መሰረት በማዘጋጀትና በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ቀናት የሚቆጠር እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 /ሶስት ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ ድረስ ዘወትር በስራ ሰአት በግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 003 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታውም በዚሁ ቀን 3፡31 ሶስት ሰአት ከሰላሳ አንድ ደቂቃ ተዘግቶ 4፡00 /አራት ሰአት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 003 ውስጥ ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታ የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም ብሄራዊ በአል ላይ የሚውል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት የሚከፈት መሆኑ ይታወቅ
- በጨረታው ተሳታፊዎች ፖስታ ላይም ሆነ ዋጋ መሙያው ላይ ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ማህተም የሌላቸው ተጫራቾች ህጋዊ ፊርማችሁን ማስቀመጥ ይኖርባችኋል።
- በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ መሞላት አለበት። ሆኖም ስርዝ ድልዝ ካለ ስለመስተካከሉ ፓራፍ መደረግ አለበት።
- መ/ቤቱ እቃዎችን 20 በመቶ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል።
- አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት በጠቅላላው ድምር ዝቅተኛ ዋጋ የሞላው ነው።
- አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ ኮሌጁ ግቢ ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
- ከዚህ በላይ ያልተጠቀሱ የጨረታ መመሪያዎች በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል።
ለበለጠ መረጃ በስቁ 0116880367/0116880630 ላይ መደወል ይችላሉ።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት
የእነዋሪ ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ
cttx Building and Finishing Materials cttx, cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Computer and Accessories cttx, cttx Construction and Water Works cttx, cttx Construction Machinery and Equipment cttx, cttx Education and Training cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Furniture and Furnishing cttx, cttx House Furniture cttx, cttx IT and Telecom cttx, cttx Materials cttx, cttx Mechanical cttx, cttx Office Furniture cttx, cttx Office Machines and Accessories cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Stationery cttx, Electromechanical and Electronics cttx