በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ በቢሾፍቱ ከተማ ለሚገኘው እንስሳት ምርምር እና እርዳታ ማዕከል በ2018 ዓ.ም ለከብቶች መኖነት የሚያገለግሉ የተለያዩ መኖዎች መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 19, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

የጨረታ ማስታወቀያ
የጨረታ ቁጥር እ/ህ/ግ/ኮ 002/2018

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ በቢሾፍቱ ከተማ ለሚገኘው እንስሳት ምርምር እና እርዳታ ማዕከል በ2018 ዓ.ም ለከብቶች መኖነት የሚያገለግሉ የተለያዩ መኖዎች ግዥ የወጣ ግልፅ ጨረታ ነው።

ስለሆነም፦

1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና ህጋዊ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸዉ እንዲሁም በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ የታክስ ከፋይ (Tin No) የምስክር ወረቀት ፤ የአቅራቢዎች ምዝገባ/ supplier list/ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር (187,508.00) አንድ መቶ ሰማኒያ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ስምንት ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ቼክ /የባንክ ዋስትና/ ማስያዝ አለባቸው::

4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00/ አምስት መቶ ብር/ በመክፈል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘዉ የእንሰሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ ግዥ ክፍል በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡

5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን የያዘውን ሰነድ አንድ ቴክኒካል ኦርጅናልና አንድ ቴክኒካል ኮፒ እና አንድ ፋይናንሽያል ኦርጅናልና አንድ ፋይናንሽያል ኮፒ በእናት ፖስታ በማድረግ ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ 16ኛዉ ቀን 7፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በኮሌጁ ግዥ ክፍል በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡

6. ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን በ7፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ8፡00 ሰዓት በግልፅ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ የህዝብ በዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለፀዉ መዝጊያ ሰዓት ታሽጎ በግልጽ ይከፈታል፡፡

7. የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይስተጓጎልም፡፡

8.ተጫራቾች የአሸነፏቸውን አቅርቦቶች በሚሰጣቸው ትዕዛዝ መሰረት በቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው የእንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ በራሳቸው ትራንስፖርት በማጓጓዝ ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ::

9. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስልክ ቁጥር፦ 011 433 8557/0912 065 392

የእንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ ቢሾፍቱ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *