በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየካ ክፍለ ከተማ የየካ መሳለሚያ ጤና ጣቢያ የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 19, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየካ ክፍለ ከተማ የየካ መሳለሚያ ጤና ጣቢያ በ2018 በጀት ዓመት በ1ኛ ዙር ግልፅ ጨረታ፡-

  1. 6211 ሎት አንድ የደንብ ልብስ የስራ ልብስ CPO 10000 (አስር ሺህ ብር )
  2. 6211 ሎት ሁለት የደንብ ልብስ የስራ ልብስ ስፌት CPO 5000 (አምስት ሺህ ብር)
  3. 6212 ሎት ሶስት አላቂ የቢሮ ዕቃዎች 6400 (ስድስት ሺህ አራት መቶ ብር)
  4. 6213 ሎት አራት የተለያዩ ህትመቶች CPO 8250 (ስምንት ሺህ ሁለት መቶ ሀምሳ ብር)
  5. 6214 ሎት አምስት አላቂ እና ቋሚ የህክምና ዕቃዎች CPO 106,258 (አንድ መቶ ስድስት ሺህ ሁለት መቶ ሀምሳ ስምንት ብር)
  6. 6218 ሎት ስድስት ሌሎች አላቂ የፅዳት ዕቃዎች CPO 8800 (ስምንት ሺህ ስምንት መቶ ብር )
  7. 6219 ሎት ሰባት ልዩ ልዩ መሳሪያዎች CPO 4500 (አራት ሺህ አምስት መቶ ብር)
  8. 6243 ሎት ስምንት የማሽነሪ እድሳትና ጥገናዎች CPO 3000 (ሶስት ሺህ ብር)
  9. 6244 ሎት ዘጠኝ የህንፃ እድሳት እና ጥገና CPO 15000(አስራ አምስት ሺህ ብር)
  10. 6256 ሎት አስር ልዩ ልዩ አገልግሎቶች CPO 2400 (ሁለት ሺህ አራት መቶ ብር)
  11. 6313 ሎት አስራ አንድ ቋሚ እቃዎች CPO 17000 (አስራ ሰባት ሺህ ብር) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል።

 በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ግለሰቦች እና ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

  • ከላይ ከተራ ቁጥር 1-10 የተጠቀሱትንና በሎት የተከፈሉትን ዕቃዎች አግባብነት ያለው ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣ የንግድ የምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ፣ በጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚችሉ በዕቃ አቅራቢዎች የተመዘገቡ እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  • ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የካ መሳለሚያ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401 በመምጣት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  • የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከላይ ከተራ ቁጥር 1-10 የተጠቀሰውን ለእያንዳንዱ ሎት በመ/ቤቱ ስም የተሰራ በ(CPO) እና በደብዳቤ ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  • አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ዕቃ ዋጋ ቫትን ጨምሮ ፋይናንሻል ኦርጂናል እና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በየሎቱ በማሸግ ሙሉ አድራሻውን በመግለጽ የካ መሳለሚያ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
  • ለ6214 ሎት አምስት ቴክኒካል፣ ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻው በፖስታ መታሸግ ይኖርበታል።
  • የጨረታ ሰነዱ የሚዘጋው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት መሆኑን እያሳወቅን የሚከፈትበት 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
  • ናሙና እንዲቀርብ በተባሉ ዕቃዎች ላይ ተጫራቾች ዋጋ ለሞሉበት ዕቃ ሳምፕል ወይም ናሙና ማቅረብ አለባቸው ናሙና ያላቀረበ ተጫራች ለዋጋ ውድድር አይቀርብም፡፡
  • ጤና ጣቢያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • የጨረታ ሰነዱ ከመመሪያው ውጭ ሁሉም ሳይገነጠል መመለስ አለበት፤ ሁሉንም የጨረታ ሰነድ ያልመለሰ መወዳደር አይችልም።
  •  ሎት 2(6211 የደንብ ልብስ ስፌት) መስፊያ ማሽን መስሪያ ቤቱ ግቢ ውስጥ አምጥቶ መስፋት የሚችል

አድራሻችን፡-ኮተቤ መምህራን ኮሌጅ አንድ ፌርማታ 200 ሜትር ወደ ውስጥ ገባ ብሎ

ለተጨማሪ መረጃ ሊቁጥር 0118656665

የየካ መሳለሚያ ጤና ጣቢያ