Your cart is currently empty!
ሲዳማ ዞን ቡራ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቋሚ የቢሮ ዕቃ፣ አላቂ የቢሮ ዕቃ እና ኤሌክትሮኒክስ ለሴክተር መ/ቤቶች የሚሆን ዕቃዎችን ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Yedebub Nigat(Oct 18, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ቡራ ወረዳ ፋ/ኢ/ ል/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በLOT3 የተለያዩ ግዦችን ለመፈጸም ስለፈለገ
- በLOT 1 ቋሚ የቢሮ ዕቃ፣
- በLOT 2 አላቂ የቢሮ ዕቃ እና
- በLOT 3 ኤሌክትሮኒክስ ለሴክተር መ/ቤቶች የሚሆን ዕቃዎችን ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት፡–
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑ ግብር የከፈሉና ፍቃድ ያደሱ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤
- የግብር ከፋይነት መለያ ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፤
- በዘርፉ በአቅራቢነት መመዝገቢያ ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ
- በፋይናንስ ህግ መሠረት 2% ዊዝሆሊድ መክፈል የሚችሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 5,000 (አምስት ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በቡራ ወረዳ ዝቅ/ጽ/ቤት ከፍለው መግዛት የሚችሉ፤
- አሸናፊ የሆነ ድርጅት በራሱ ወጪ ዕቃውን አጓጉዞ እስከ ቦታው ድረስ ማምጣት የሚችሉ፤
- መ/ቤቱ ዕቃውን የሚገዛውን አይተም በአይተም ነው፣
- ጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን ኦርጅናል ኮፒ በሰም ታሽጎ በሁሉም ዶክመንት ላይ ህጋዊ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 በተከታታይ ስራ ቀናት የሚቆይ ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 5፡30 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 6፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ6ኛው ቀን ቡራ ወረዳ ፋ/ኢ/ልጽ/ቤት በቢሮ ቁጥር 8 ይከፈታል፤
- የገበያ ዋጋ ያላገናዘበ ጨረታ ተቀባይነት አይኖረውም፤
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
- ጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁር 09 26 652 283
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምስራቃዎ ሲዳማ ዞን ቡራ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Computer and Accessories cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Furniture and Furnishing cttx, cttx House Furniture cttx, cttx IT and Telecom cttx, cttx Office Furniture cttx, cttx Office Machines and Accessories cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Stationery cttx, Electromechanical and Electronics cttx