ሕብረት ባንክ አ.ማ. ለሰጠዉ ብድር በመያዣነት የያዘዉን ንብረት በግልጽ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል


Reporter(Oct 19, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

የሐራጅ ማስታወቂያ፤

ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቅርንጫፉ በኩል ለሰጠዉ ብድር በመያዣነት የያዘዉን ከዚህ በታች የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልጽ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡

ተራ .

የተበዳሪ ስም

የአስያዥ ስም

አበዳሪው ቅርንጫፍ

 የሰሌዳ ቁጥር

የተሽከርካሪ አይነት

የስሪት ዘመን

የሻንሲ ቁጥር

የሞተር ቁጥር

የሐራጅ መነሻ ዋጋ (... ሳይጨምር)

ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት

1

ሬድሮክ ትሬዲንግ /የተ/የግ//

ሬድሮክ ትሬዲንግ /የተ/የግ//

ቦሌ መድሃኒአለም

 

አአ-03-B16263

 

ጃፓንሊንከሊንአውቶሞቢል

2020/..

 

5LMJJ2LT7LEL06793

 

LEL06793

 

15,650,000.00

 

ጥቅምት 25 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 400 እስከ 500 ሰዓት

2

ሬድሮክ ትሬዲንግ /የተ/የግ//

ሬድሮክ ትሬዲንግ /የተ/የግ//

ቦሌ መድሃኒአለም

 

አአ-03-B15111

እንግሊዝሬንጅሮቨርየመስክ ተሽከርካሪ

2020/..

 

SALGA2BU1LA407727

 

LA407727

15,350,000.00

ጥቅምት 25 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 500 እስከ 600 ሰዓት

የሐራጅ ደንቦች፡-

1.  ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በሕብረት ባንክ አ.ማ.(Hibret Bank S.C) ስም የተሰራ የባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡ከባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) ውጭ የሚቀርብ የጨረታ ማስያዣ ተቀባይነት የለውም፡፡

2. ተሽከርካሪዎቹን ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከባንኩ የሕግ አገልግሎቶች መምሪያ ወይም ከቅርንጫፉ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ዕለት ሶስት ቀናት አስቀድሞ መጎብኘት ይችላል፡፡

3. ተሽከርካሪዎቹ ቀረጥ ሳይከፈልባቸው ወደአገር ውስጥ የገቡ ናቸው፡፡

4. የመኪናዎች ሐራጅ የሚካሄደው የሕብረት ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ(ሕብር ታወር) 26ኛ ፎቅ የሕግ አገልግሎት መምሪያ ባለው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ነው፡፡

5. በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ተበዳሪ እና አስያዥ ብቻ ናቸው፡፡ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል፡፡ተጫራቾች የሕግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ሕጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ሰው ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ፅ/ቤት ወይም በተመሳሳይ አካል የፀደቀ መመስረቻ ፅሁፍ(የመተዳደሪያ ደንብ)፣ቃለ ጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት፡፡

6. የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይደረጋል፡፡

7. ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡ከፍተኛ ዋጋ ለሰጠ ተጫራች ደግሞ ያቀረበውን ዋጋ ባንኩ ሲቀበለው ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ እንዲከፍል የሚገልፅ ደብዳቤ የሚሰጠው ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል፡፡በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡

8. የጨረታው አሸናፊ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች የጨረታ አሸናፊ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን ይከፍላል፡፡

9.  ባንኩ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

10.  ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር የሕግ አገልግሎቶች መምሪያ 0115 57 37 72/0114 70 41 03 ወይም 0114 70 03 15 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *