ሳምሶን ቸርነት (ኢርኮ ቴክስታይል እና ጋርመነት) ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ የተለያዩ አልባሳትን በጨረታ መሸጥ ይፈልጋል


Reporter(Oct 19, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

Ref.SCHB/FDM/7434/01/25

የአልባሳት ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

ሳምሶን ቸርነት (ኢርኮ ቴክስታይል እና ጋርመነት) ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ የተለያዩ አልባሳትን በጨረታ መሸጥ ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተመለከቱ መስፈርቶችን የምታሟሉ ደንበኞች በጨረታዉ እንድትካፈሉ ይጋብዛል፡

  1. በዘርፍ የታደሰ ንግድ ፈቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን አለባቸዉ።
  2. ጨረታ ማስከበሪያ በሳምሶን ቸርነት በዳዳ ስም የተዘጋጀ የሚገዙበትን ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነድ ጋር በፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  3. እቃዎችን ማየት የሚፈልግ ማንኛዉም ተጫራች ፋብሪካዉ በሚገኝበት አዳማ ከተማ በመቅረብ ማስታወቂያዉ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 300 እስከ 900 ድረስ ብቻ መመልከት የሚችሉ መሆኑን እናሳዉቃለን።
  4. ተጫራቾች ጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያዉ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስረኛዉ ቀን ከቀኑ 800 ሰዓት ድረስ ብቻ በጨረታ ሰነዱ ላይ ባለዉ ዋጋ ማቅረቢያ መሰረት የሚገዙበትን ዋጋ አዲስ አበባ ፊጋ መብራት ወደ ጎሮ በሚወስደዉ 200 ሜትር ቲጂ ኮሜርሻያል ወደ ቀኝ ታጥፈዉ ዋና መስሪያ ቤት በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ጨረታዉ በአስራ አንደኛዉ ቀን ከቀኑ 830 አዳማ ይከፈታል:: ነገር ግን ተጫራቾች በራሳቸዉ ምርጫ በመክፈቻዉ ቀን ሰዓትና ቦታ ሳይገኙ ቢቀሩም ጨረታዉ የሚከፈት ይሆናል።
  6. ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸዉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በጨረታዉ ያሸነፉበት ጥቅል አልባሳት ዋጋ 5 ቀናት ከፍሎ 10 ቀናት ዉስጥ አልባሳቱን የማንሳት ግዴታ አለባቸዉ።
  7.  በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ በመመርኮዝ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
  8. ድርጀቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጫረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።

ስለሆነም በዚህ መስረት ለመጫረት ፍላጎት ያላቸዉን ህጋዊ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ሳምሶን ቸርነት (ኢርኮ) ቴክስታይል እና ጋርመንት ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ዋና መስሪያ ቤት ፋይናንስ ቢሮ ቀርበዉ የጨረታ ሠነዱን በመዉሰድ መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

ማሳሰቢያ፡ከተጠቀሰዉ ሰዓት እና ቀን ዘግይቶ የሚመጣ የማንኛዉም ተጫራች ሰነድ ተቀባይነት አይኖረዉም።

ለበለጠ መረጃበስልክ ቁጥር +251944362222/+251944352222 ይደዉሉ

አድራሻ፡አዲስ አበባ ፊጋ መብራት ወደ ጎሮ በሚወስደዉ

200 ሜትር ቲጂ ኮሜርሻያል ወደ ቀኝ ታጥፈዉ

ወደ ዉስጥ ገባ ብሎ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *