የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለሥልጣን መስሪያ ቤት 5000 /አምስት ሺህ/ ሊትር የሚይዝ የነዳጅ መቅጃ ቦቲ እና ደብል ካፕ መኪና ኪራይ አገልግሎት ግዢ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 21, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለሥልጣን መ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ከካፒታል በጀት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል

  • 5000 /አምስት ሽህ ሊትር የሚይዝ የነዳጅ መቅጃ ቦቲ በሎት 1/አንድ/ እና ዳብል ካፕ መኪና ኪራይ አገልግሎት ግዢ በሎት 2 /ሁለት/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት የምትችሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

  1. በዘመኑና በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው፣
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN NO) ያላቸው እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (T) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው
  4. ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ሲሆን ተጫራቾች የጨረታ ማሰከበሪያ ዋስትና (BID WOND) ብር የምሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በማስላት ለእያንዳንዱ ሎት ለየብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ ማቅረብ አለበት።
  5. ማንኛውም ተጫራች ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ በሚጠይቀው የዋጋ አሞላል ብቻ መሙላት አለበት። በሚጠይቀው ዋጋ አሞላል ካልሞተ የጨረታ ሰነዱ ውድቅ ይሆናል ።
  6. አሸናፈው የሚለየው በእያንዳንዱ ሎት ድምር ዋጋ ይሆናል
  7. የነዳጅ ቦቲ ታንክሩ ለሚይዘው ናፍጣ ዋስትና የሚሆን ማስያዣ ማቅረብ የሚችል፡
  8. የሚቀርበው የዳብል ካፕ መኪና ስሪት ዘመን እ.ኤ.አ ከ2009 በኋላ መሆን አለበት
  9. ተጫራቾች ጨረታ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኪሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
  10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር በመክፈል ከግ/ፋይ/ን/ አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 508 ማግኘት ይችላሉ።
  11. ጨረታው አየር ላይ የሚቆው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ11/02/2018 ዓ/ም እስከ 25/02/2018 ዓ/ም 11፡30 ድረስ መግዛት ይችላሉ።
  12. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ መንገዶች ባለስልጣን መ/ቤት በግዥና/ፋይ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 508 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 26/02/2018 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  13. ጨረታው ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ፋይን ስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 508 በ26/02/2018 ዓ/ም 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ላይ ይከፈታል። ነገር ግን ዉረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እሁድና የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን።
  14. ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  15. ለበለጠ መረጃ በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን መ/ቤት በአካል በመቅረብ ወይንም በስልክ ቁጥር 033 351 33 37,033 551 05 04 መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
  16. ማሳሰቢያ፡- ሁሉም ተጫራቾች በተጫራቾች መመሪያ መሰረት የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈጸም ቃል የሚገቡበትን ቅጽ ፈርሞ የድርጅቱን ማህተም በመምታት ጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት አለበት።

የመስሪያ ቤቱ አድራሻ ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ሕንጂ አምስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 508 ላይ ነው።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለሥልጣን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *