በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ የአዳራሽ መድረክና የመድረክ ጀርባ ኢንቲሪየር ዲዛይን ስራ እና የአዳራሽ ጠረጴዛ ተከላ አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ማሰራት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 22, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 06/2018

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ በመደበኛ ከዚህ በታች በሎት የቀረበውን ስራ ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ የአዳራሽ መድረክና የመድረክ ጀርባ ኢንቲሪየር ዲዛይን ስራ እና የአዳራሽ ጠረጴዛ ተከላ ከዚህ በላይ ለተዘረዘሩት በውድድር ለመሣተፍ የሚፈልጉ፡

  1. በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው
  2. ተጫራቾች ዋጋቸውን የሚገልፀውን ሰነድ በታሸገ ፖስታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ ከግ/ፋ/ን/ አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በአካል በመቅረብ መግዛት አለባቸው!
  3. የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00-6፡00 ድረስ ብቻ ለዚህ አላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን 9፡00 ሰዓት ይከፈታል፣ ሆኖም 16ኛው ቀን የሰራ ቀን በማይሆንበት ጊዜ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀስው ጊዜና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  5. የእቃው ጠቅላላ ሽያጭ ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢዎች ብቻ መጫረት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለ 90 ቀን ጸንቶ የሚቆይ ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ ብቻ በሲፒኦ ወይም እንኮንድሽናል ባንክ ጋራንቲ ማቅረብ አለባቸው፤
  7. ጨረታው ለ2 ወራት /60 ቀናት ብቻ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል።
  8. የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ማግኘት ይቻላል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
  9. ቢሮው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡- ሽያጩ ቫትን ጨምሮ ከብር 20000.00 /ሀያ ሺህ ብር በላይ ለሆነው ግዥ 50% ቫት ቀንን የምናስቀር መሆኑን እንገልፃለን፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 046-221-7002/3

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ሀዋሳ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *