Your cart is currently empty!
በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ጽ/ቤት የተለያዩ ለፋብሪካ አገልግሎት የሚውሉ የቤት ውስጥ መገልገያ እቃዎች እና የአደጋ መከላከያ አልባሳት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 22, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ቁጥር፡-LP/OI/023/
OKSF1&3/2018
በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ጽ/ቤት የተለያዩ ለፋብሪካ አገልግሎት የሚውሉ የቤት ውስጥ መገልገያ እቃዎች እና የአደጋ መከላከያ አልባሳት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
1. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ስነድ ጋር ህጋዊ የታደሰ አዲስ የንግድ ፈቃድ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የምስከር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፤ በተጨማሪም ተጫራቾች የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ መረጃ ማቅረብ አለባቸው ::
2. ተጫራጮች የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከሚመለከተው አድራሻ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ ከሰዓት በፊት ከ2፡30-6፡00፣ ከሰዓት ከ7፡00-10፡30 እና ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2፡30-6፡00) ቀጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ ገዝተው በጫረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ
የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ
ግዥ ቡድን (ማስተባበር ቢሮ)
አድራሻ፡- ኮልፌ ቀራኒዮ፣
ከጦር ሃይሎች ወደ ዘነብ ወርቅ በሚወስደው መንገድ
በተለምዶ 3 ቁጥር ማዞርያ / ቶታል ገባ ብሎ
የፌድራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ህንፃ ላይ
ሕ-B ቢሮ ቁጥር 1371/125 ፎቅ
የስልክ ቁጥር (አድራሻ)+251-91 354 4731+251 92 613 8885/+251-91 617 0834
አዲስ አበባ
3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው የቤት ውስጥ መገልገያ እቃዎች እና የአደጋ መከላከያ አልባሳት የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይም በቅድመ ሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንከ ጋራንቲ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለጨረታው በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው 24/02/2018 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን 24/02/2018 ዓ.ም ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡
5. የጨረታው ዋጋ ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ30 ቀናት ነው ፡፡
6. የጨረታው ማስረከቢያ ዋስትና ፀንቶ የመቆያ ጊዜ ለ 60 ቀናት ነው፡፡
ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ ጽ/ቤት