በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የእንስሳት እና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ በዚህ በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ የህትመት አገልግሎት ሥራ እና የመስተንግዶ አገልግሎት ግዥ በአገር ውስጥ ገበያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 22, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የእንስሳት እና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ በዚህ 2018 በጀት ዓመት የተለያዩ የህትመት አገልግሎት ሥራ እና የመስተንግዶ አገልግሎት ግዥ በአገር ውስጥ ገበያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለጹትን ነጥቦች ማሟላት ይኖርበታል፡፡

1. ተጫራቾች ግዴታ ማሟላት ያለባቸው የቅድሚያ መወዳደሪያ መስፈርቶች ማለትም፡

1.1 በዘርፉ የዘመኑ የታደሠ ንግድ ፈቃድ

1.2 የንግድ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬትያለው

1.3 ንግድ ፈቃድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያለው

1.4 የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ

1.5 ሲፒኦ

1.6 የጨረታ ሰነድ ግዥ የፈጸመ እና

1.7 የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያለው ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስወቂያ በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታውን ሰነድ በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የእንስሳት እና ዓሳ ሃባት ልማት ቢሮ በግዥ ፋይ ንብ/አስ ደጋፊ ዳይሬክተር የስራ ሂደት ክፍል ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቾች በእያንዳንዱ በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነዶች ላይ ተጫራቾች ወይም የህጋዊ ወኪል ፊርማና ማህተም ማኖር ይኖርባቸዋል፡፡

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና /Bank Guarantee / ለውድድር የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 40,000.00/አርባ ብር ብቻ በሲ.. (C.P.O) ወይም bid Bond የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል :: የጨረታ ተወዳዳሪዎች በውድድሩ ከተሸነፉ ለዋስትና ያስያዙት የጨረታ ማስከበርያ ዋስትናና እንዲሁም ናሙና የጨረታው ውጤት ታውቆ ውል ከተፈራረመ ቡኃላ ወድያውኑ የውል ማስከበርያው ይመለስላቸዋል፡፡

5. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርቡትን የውድድር ጥያቄ /ቤቱ ይቀበልም፡፡

6. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሆኖ 15ኛው የስራ ቀን 400 ሰአት የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋ ሲሆን በእለቱ 430 ሠአት ፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የእንስሳት እና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

7. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

8. ለተጨማሪ መረጃ በቢሮው ስልክ ቁጥር 09-12-97-77-98 ደውለው ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የእንስሳት እና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ

ሠመራ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *