Your cart is currently empty!
ቡና ባንክ አ.ማ. መኪና በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Reporter(Oct 22, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የሐራጅ ማስታወቂያ
ቁጥር፣ ቡባ/ሕአዳ/ሐራጅ/05/2018
ቡና ባንክ አማ በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ቀጥሎ የቀረበውን ንብረት በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
| ተ.ቁ | የተበዳሪ ስም | የንብረት አስያዥ ስም | አበዳሪ ቅርንጫፍ 
 | የሰሌዳ ቁጥር 
 | የመያዣ አይነት/ሞዴል | የሻንሲ ቁጥር/ሴሪያል ቁጥር | የሞተር ቁጥር 
 | የጨረታ መነሻ ዋጋ በብር 
 | የጨረታ ቀን እና ሰዓት | ጨረታው የወጣው | |
| ቀን | ሰዓት | ||||||||||
| 1 | አቶ አሰፋ ዘሪሁን አደመ | ተበዳሪ | ቦሌ 18 | ኢት-03-80669 | የ2016 ምርት ሲኖ ትራክ | LZZ5ELN B7FD117238 
 | WD615.69* 151007026067* 
 | 3,900,000.00 
 | ጥቅምት26 ቀን 2018 ዓ.ም 
 | 4፡00-5፡00 | ለመጀመሪያ ጊዜ 
 | 
| ኢት– 03-94080 | የ2017 ምርት ሲኖ ትራክ | LZZ5BLS F2HA256679 
 | WD615.47*1 70607031337* 
 | 7,000,000.00 
 | ጥቅምት 26 ቀን 2018 ዓ.ም 
 | 5:00-6:00 
 | ለአምስተኛ ጊዜ 
 | ||||
| 2 | ወ/ሮ ጠየቅ የቆየ ተረፈ | ተበዳሪ | ወሎ ሰፈር | ኢት -03-A15972 | የ2021ምርት ቻይና ሲኖ ትራክ 
 | LZZ5BBF F8ME903321 
 | YC4E160.33 E3717M00240 
 | 2,750,000.00 
 | ጥቅምት 26 ቀን 2018 ዓ.ም | 8:00-9:00 | ለመጀመሪያ ጊዜ | 
የሐራጅ ደንቦች፣
- ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4ኛ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.አ.) ብቻ በቡና ባንክ አ.ማ ስም በማስራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ::
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ አሸናፊ መሆኑ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ባሉት በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ ተጠቃሎ መከፈል አለበት:: ካልተከፈለ የተያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል:: በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃሉ:: ላላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ በዕለቱ ይመለስላቸዋል::
- በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና ንብረት አስያዥ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ብቻ ናቸው:: ተበዳሪ እና ወኪሎቻቸው ባይገኙም ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል::
- የተጫራቾች ምዝገባ ከእያንዳንዱ የንብረት ሐራጅ መዝጊያ ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል:: በሐራጁ የመጨረሻ ሰላሳ ደቂቃዎች የተጫራች ምዝገባ አይካሄድም::
- የሐራጁ አሸናፊ ገዢ/ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን፣ ግብር በዋጋው ላይ የሚታሰብ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) ካለ ከስም ማዛወሪያ ክፍያ ጋር የተገናኙና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ታክስ እና ግብሮች ገዥው አሸናፊው ይከፍላል::
- በሐራጁ የተዘረዘሩትን ንብረቶች ለማየት ከአበዳሪ ቅርንጫፉ ጋር በመነጋገር ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ይቻላል::
- ተጫራቹ የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው አሸናፊነቱን የሚገልፅ ደብዳቤ በጽሑፍ ሲደርሰው ብቻ ነው::
- ጨረታው በቡና ባንክ ኢማ ዋናው መስሪያ ቤት ቦሌ ክፍለ ከተማ፣ ከወሎ ሰፈር አደባባይ ወደ ቦሌ ሲሄዱ ሩዋንዳ መታጠፊያ ሳይደርሱ በሚገኘው የባንኩ ሕንፃ 9ኛ ፎቅ በሚገኘው አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል::
- የብድር መስፈርት ለሚያሟሉ ተጫራቾች ባንኩ ብድር ያመቻቻል
- ባንኩ የተሻለ አማረጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ ‘ ሕግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ስ.ቁ 011-1-58-08-63/011-1-26-36-09፣ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።