Your cart is currently empty!
ወጋገን ባንክ አ.ማ. ተሽከርካሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Reporter(Oct 22, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ
ቁጥር ወጋገን 004/2018
ወጋገን ባንክ አማ በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 መሰረት ከዚህ በታች የቀረቡትን የመያዣ ንብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
| ተ.ቁ | የተበዳሪው ስም | የንብረት አስያዥ ስም | አበዳሪ ቅርንጫፍ | የተሸከርካሪ ዓይነት | የሰሌዳ ቁጥር | የቫንሲ/ሴሪያል ቁጥር | የሞተር ቁጥር | ዘመን | የነዳጅ አይነት | የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር | ጨረታው የሚከናወንበት ቀን | |
| ቀን | ሰዓት | |||||||||||
| 1 | ዮቴክ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር | ዮቴክ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር | ጎፋ | ፎርድ ፒክ አፕ | አአ-3-38253 | MNCBSBE 806W525027 | W9AT-171340 | 2006 | ናፍጣ | 300,000.00 | ጥቅምት 27 ቀን 2018 ዓ.ም. | ከጧቱ 3፡00-6:00 
 | 
| ባክ ሎደር | LD-0375 | ESMJ00550 | CAS32750 | 2006 | ዲዝል | 1,500,000.00 
 | ||||||
ማሳሰቢያ
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4 (አንድ አራተኛ) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (CPO) በወጋገን ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት በጨረታው ዕለት በመቅረብና በመመዝገብ በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ።
- የጨረታ አሸናፊ ከባንኩ የብድር ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ከተሰጠው ቀን ጀምሮ ቀሪውን ገንዘብ በ15 /አስራ አምስት ቀናት ውስጥ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል:: ባይከፍል ግን የሐራጁ ውጤት ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፣ ላላሸነፉት ተጫራቾች ግን ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያዉኑ ይመለስላቸዋል።
- የተጫራቾች የምዝገባ ሰዓት ከጧቱ 3፡00 – 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ሲሆን ከ4፡00-6፡00 ሰዓት የጨረታው ጊዜ ይሆናል:: ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኋላ ለእያንዳንዱ ንብረት የሚመደበው የጥሪ ስዓት 30 ደቂቃ ብቻ ነው:: ሆኖም የጨረታው መጠናቀቂያ ሰዓት ድረስ አሸናፊው ካልተለየ አሸናፊ እስኪለይ ድረስ ጨረታው ይቀጥላል።
- በጨረታው የተሻለ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ጨረታውን ካካሄደው ከባንኩ የብድር ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ሲደርሰው ብቻ አሸናፊ ይባላል።
- ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል።
- ጨረታው የሚካሄደው፡ በባንኩ ዋና መ/ቤት 13ኛ ወለል ላይ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ የሚካሄድ ይሆናል።
- ለሀራጅ ጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች የጨረታው ቀን ከመድረሱ በፊት ከታች በተጠቀሰዉ ስልክ ቁጥር በመደወል ከባንኩ ጋር ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይችላል።
- ተበዳሪው ንብረት አስያዥ/ ወይም ሁለቱም በጨረታው ቀን እና ሰዓት በቦታው ላይ መገኘት ይችላሉ:: ነገር ግን ተበዳሪው ንብረት እስያዡ በጨረታ ቀን እና ሰዓት በቦታው ባይገኝ ጨረታው በሌለበት ይካሄዳል:: ከዚህ በተጨማሪ ጨረታው ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ወይም የተጫራቾች ህጋዊ ተወካዮች ብቻ ናቸው።
- ማንኛውንም ለመንግስት ሊከፈል የሚገባውን ክፍያ ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ሙሉ በሙሉ የጨረታው አሸናፊ የሚከፍል ይሆናል።
- ለበለጠ ማብራሪያ ወይም የጉብኝት ቀጠሮ ለማመቻቸት በወጋገን ባንክ ኢማ የብድር ማስመለስ ዳይሬክቶሬት፡ 011-558-18-37፣ መደወል ይችላሉ።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም።
ወጋገን ባንክ አማ