Your cart is currently empty!
በሲዳማ ብ/ክ/መ/ እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ የሀዋሳ ዳልጋ ከብት አባላዘር ማምረቻ ማቀነባበሪያና ማሰራጫ ማዕከል የአባላዘር ላብራቶሪ አላቂና ቋሚ ዕቃዎች፣ IVECO ከባድ መኪና ጥገና እና የቢሮ ወለል ምንጣፍ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 24, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 04/18
በሲዳማ ብ/ክ/መ/ እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ የሀዋሳ ዳልጋ ከብት አባላዘር ማምረቻ ማቀነባበሪያና ማሰራጫ ማዕከል በ2018 በጀት ዓመት ህጋዊ ዕውቅና ካላቸው ድርጅቶች ከታች የተዘረዘሩ ዕቃዎችን እና አገልግሎቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- LOT1.የአባላዘር ላብራቶሪ አላቂና ቋሚ ዕቃዎች፣
- LOT2. IVECO ከባድ መኪና ጥገና እና
- LOT3. የቢሮ ወለል ምንጣፍ
በመሆኑም በንግድ ዘርፉ የታደሰ ፍቃድ ፣ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማስረጃ እና የአቅራቢነት ምዝገባ ወረቀት የሚያቀርቡ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለመጫረት የሚያቀርቡትን ጠቅላላ ዋጋ 1% ገንዘብ የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች በቢሮው የተዘጋጀውን የተጫራቾች መመሪያና ዝርዝር መግለጫ | ስፔስፊኬሽን/ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 9፡00 ሰዓት ድረስ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከማዕከሉ ግዢ ፋይ/ንብ/አስ/ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ ፕሮፎርማ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛ ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ የቴክኒካል እና የፋይናንሻል ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ እያዳንዳቸው በተለያየ ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እና CPO ቴክኒካል ዶክሜንት ውስጥ በማድረግ አጠቃላዩን በአንድ ፖስታ በማሸግ በማዕከሉ ግዢ ፋይ/ንብ/አስ/ቢሮ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- የጨረታውን ሳጥን የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛ ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 9፡05 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ተወካዮቻቸው በተገኙበት በማዕከሉ የግዢ ፋይ/ንብ/አስ/ቢሮ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ባይሆን ሳጥኑን የማሸጉም ሆነ የመከፈቱ ሥነ-ሥርዓት የሚከናወነው በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓትና ሁኔታ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጊዜ ወይም በቦታው ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያስተጓጉልም፡፡
- ማዕከሉ ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በዚህ ስልክ ቁጥር 046 212 9501/ 046 212 9504 ይደውሉ።
የሀዋሳ ዳልጋ ከብት አባላዘር ማምረቻ፣ ማቀነባበሪያና ማሰራጫ ማዕከል
cttx Carpets and Curtains cttx, cttx Furniture and Furnishing cttx, cttx Health Care, cttx Health Related Services and Materials cttx, cttx Laboratory Equipment and Chemicals cttx, cttx Maintenance and Repair cttx, cttx Medical Equipment and Supplies cttx, cttx Others cttx, cttx Vehicle (garage service) cttx, Medical Industry cttx