የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋኢ/ል/ጽ/ቤት በዋን ዋሽ በጀት ድጋፍ በደቡብ ቤንች ወረዳ በደቻባስ ቀበሌ በደቻባስ ጤና ኬላ ቅጥር ግቢ ውስጥ ባለ አራት ቀዳዳ ሽታ አልባ ሽንት ቤት ግንባታ በጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 24, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋኢ/ል/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በወረዳው በጤና ጽ ቤት በዋን ዋሽ በጀት ድጋፍ በደቡብ ቤንች ወረዳ በደቻባስ ቀበሌ በደቻባስ ጤና ኬላ ቅጥር ግቢ ውስጥ ባለ አራት ቀዳዳ ሽታ አልባ ሽንት ቤት ግንባታ በጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

  1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፣
  2. ደረጃ 8 (ስምንት) እና ከዚያ በላይ የሆነ ማህበር ተቋራጭ።
  3. የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል /የምትችል።
  4. የዘመኑን ግብር የከለለች እና ክሊራንስ ከግብር መ/ቤት ያቀረበ፣
  5. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(ቲን ነምበር) ማቅረብ የሚችል /የምትችል።
  6. ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ እና ኮፒውን አያይዞ ማቅረብ የሚችል የምትችል።
  7. የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል /የምትችል።
  8. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዶች ጋር የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ የሚችሉ።
  9. የታደሰ ህጋዊ ሰውነት የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
  10. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በአሃዝ እና በፊደል መግለጽ አለባቸው። በፊደል እና በአሃዝ መካከል ልዩነት ካለው በፊደል የተገለጸው ይወሰዳል።
  11. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር ሶስት መቶ (300) በመክፈል ከደ/ቤ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10/ አስር/ በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  12. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ፋይናንሻል አንድ(1) ኦርጅናል እና ሁለት(2) ኮፒ እንዲሁም ቴከኒካ አንድ(1) ኦርጅናል እና ሁለት(2) ኮፒ ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  13. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ ወይም ያላካተተ መሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡ ያለበለዚያ ያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
  14. ተጫራቾች በእያንዳዱ ሰነድ ላይ ፊርማቸውን እና የድርጅታቸውን “ማህተም ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
  15. ተጫራቾች የጨረታ ፖስታውን በደ/ቤ/ወ/ፋ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  16. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21(ሃያ አንድ) የስራ ቀናት ከፍት ሆኖ በ21ኛው ቀን ከሰዓቱ 9:00 ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን ከቀኑ 9:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል ፣ እለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

ማሳሰቢያ፦

  1. ተጫራቾች የማህበሩ አባላት ስለመሆናችው የስም ዝርዝር ከነ ስራ ኃላፊነታቸው የሚገልጽ ከአደራጅ መ/ቤት ለደ/ቤ/ወ/ፋ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት አድራሻ የተጻፈ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  2. የግንባታ ዲዛይን የሚቀርብ ይሆናል፡፡

መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ ፡- የደ/ቤ/ክ/ፋ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት

ደ/ወርቅ ስልክ፡-09 66 88 69 73 / 09 10 99 77 47/ 09 29 24 17 31 በመደወል መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ።

የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *