Your cart is currently empty!
የፈዲስ ግብርና ምርምር ማዕከል ለ2018 የመኪና መለዋወጫ፣ የፅህፈት መሳሪያ፣ ቋሚ እቃዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የመኪና ጎማዎች፣ ኤሌክትሮኒክሶች እና ጥሬ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 24, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የፈዲስ ግብርና ምርምር ማዕከል ለ2018 የመኪና መለዋወጫ፤ የፅህፈት መሳሪያ ቋሚ እቃዎች ፤ የፅዳት እቃዎች፣ የመኪና ጎማዎች ፤ ኤሌክትሮኒክሶች እና ጥሬ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫረቾች ፡–
1. በሚወዳደሩበት ዘርፍ የዘመኑ ግብር የከፈሉ እና የተሟላ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
2. ግብይቱ ከ200,000 (ሁለት መቶ ሺህ )ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
3. ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የንግድ ምዝገባ ቁጥር ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
4. ተጫራቾች በሚያቀርቡበት ሃሳብ መስጫ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር ይኖርባቸዋል።
5. የጨረታ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች የመወዳዳሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም።
6. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ ሆኖ ለወደፊት በመንግስት ለሚያወጣው ጨረታ እዳይሳተፉ ሊደረግ ይችላል።
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200 ብር ብቻ በመክፈል ከፈዲስ ግብርና ምርምር ማዕከል መግዛት ይችላሉ።
8. የሚገዙትን ማቴሪያሎች ዝርዝር መግለጫ ከሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን ብቻ ለብቻ ከሁሉም የንግድ ማስረጃዎቻቸው ጋር በታሽገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው።
10. ተጫራቾች ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታተይ ለ15 የስራ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን 4፡00 ላይ ተዘግቶ 4፡30 ላይ ይከፈታል።
11. 50,000 የባንክ ጋራንቲ ሲፒኦ ማስያዝ የሚችል።
12. የጨረታ ማስተባበያ ሰዓት ካለፈ በኋላ የመጣ የጨረታ ሰነድ ከጨረታ ሳጥን ውስጥ ሳይገባ ተመላሽ ይሆናል።
13. መስሪያ ቤቱ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳስቢያ፡– መስሪያ ቤቱ ግዥውን በነጠላ ዋጋ ወይም በሎት ሊያወዳድር ይችላል።
ለበለጠ መረጃ በስ.ቁ 025 666 7549 / 025 666 7550 መጠየቅ ይችላሉ።
አድራሻ፡– ከሐረር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 500ሜ ገባ ብሎ
በምስራቅ ሐረርጌ የፈዲስ ግብርና ምርምር ማዕከል