የሲዳማ ብ/ክ/መንግሥት ርዕሰ መስተዳደር ጽህፈት ቤት በ2018 በጀት ዓመት የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት ዕቃ፣ ጃኩዚ ስቲም እና የሻወር አገልግሎት የሚሰጥ ባዝታብ ከነሙሉ አክሰሰሪ እና ፈርኒቸር (ሮያል ኪንግ መጠን ያለው በእጅ የተሰራ ወንበር) ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 25, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የሲዳማ //መንግሥት /መስተዳደር /ቤት 2018 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከዚህ በታች የተመለከተዉን

  • ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ
  • ሎት 2 የጽዳት ዕቃ
  • ሎት 3 ጃኩዚ ስቲም እና የሻወር አገልግሎት የሚሰጥ ባዝታብ ከነሙሉ አክሰሰሪ
  • ሎት 4 ፈርኒቸር (ሮያል ኪንግ መጠን ያለው በእጅ የተሰራ ወንበር) ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫቾች ከዚህ በታች በዝርዝር የተመለከቱ ሁኔታዎችን በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡

1. በዘርፉ በተሰማሩበት ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑ የመንግሥት ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል

2. በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገበበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤

3.የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ማቅረብ የሚችል

4.በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው ማስረጃ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ

5.የመወዳደሪያ ዋጋው ቫትን ጨምሮ በግልፅ መፃፍ አለበት

6. የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት በባንክ በተረጋገጠ cpo 20,000 (ሃያ ) ብር ማስያዝ አለባቸው።

7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ከተራ ቁጥር 1-4 ድረስ ላሉ ሎት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ የታደሰ ንግድ ፍቃድና ተያያዥነት ያላቸው ሰነዶች ኮፒ ይዞ በመቅረብ ከግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቀርበው ሰነዱን መግዛት ይችላል።

8. የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መመሪያ መሰረት ተሞልቶ ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ በሰም በታሸገ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ከተውና በሁሉም ዶክመንት የድርጅቱን ማህተም በመምታትና በመፈረም ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት 16ኛው ቀን ከጠዋቱ እስከ 500 ሰዓት ድረስ ለዚህ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀን በሲዳማ //መንግስት ርዕሰ መስተዳደር /ቤት 530 ላይ ይከፈታል።

10.የጨረታ አሸናፊ ያሸነፉበትን ዕቃ እስከ ሲዳማ //መንግስት ርዕሰ መስተዳድር /ቤት ቢሮ በማቅረብ ያስረክባል፡፡ አስቀድሞ የዕቃውን ናሙና ማቅረብ ይኖርበታል።

11. ጨረታው የሚከፈትበት የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ ዝርዝር የጨረታ ሂደት በጨረታው ሰነድ መመሪያ ላይ ተገልጧል።

ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለ መረጃ

ስልክ ቁጥር– 046-212-4290/91

የሲዳማ //መንግሥት /መስተዳደር

/ቤት