በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ እና ክህሎት ቢሮ የቂርቆስ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የተለያዩ ቋሚና አላቂ የሥልጠና ግብአቶች፣ ቋሚ የቢሮ መገልገያዎች፣ አላቂ የቢሮ መገልገያዎች፣ የደንብ ልብስ እና የፅዳት እቃዎችን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 25, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

የጨረታ ማስታወቂያ 

የጨረታ ቁጥር KMC/OT/001/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ እና ክህሎት ቢሮ የቂርቆስ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የተለያዩ ቋሚና አላቂ የሥልጠና ግብአቶች ቋሚ የቢሮ መገልገያዎች፣ አላቂ የቢሮ መገልገያዎች የደንብ ልብስ እና የፅዳት እቃዎችን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ የሀገር ውስጥ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መመሪያዎች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

የጨረታ መስፈርቶች

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት የቫት የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ አግባብነት ያለው የአቅራቢዎች የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው፡፡
  2. ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ ከተደራጁበት /ከተማ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት /ቤት መሳተፍ እንዲችሉ የሚገልፅ ማስረጃ ከተደራጁበት የተፃፈ የድጋፍ ደብዳቤ ለጨረታ ማስከበሪያ እና ለውል ማስከበሪያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች በዝርዝር ላቀረቧቸው እቃዎች ናሙና ስለሚያስፈልጋቸው የጨረታ ሳጥኑ ከመከፈቱ በፊት እስከ 10ኛው ቀን ከቀኑ 1130 ድረስ ጥራታቸው እንዲረጋገጥ ሰነዱ ላይ በቀረበው መሰረት ናሙና ማቅረብ አለባቸው ፡፡ ቀኑ ካለፈ የሚመጣ ናሙና ተቀባይነት የለውም።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሚያስረክቡበት ጊዜ የሚወዳደሩበት ዕቃ ለቋሚና አላቂ የስልጠና ግብአቶች 80,000 ብር/ሰማኒያ ሺህ/ ብር ለቋሚ የቢሮ መገልገያዎች 90,000.00 /ዘጠና ሺህ/ ብር ለአላቂ የቢሮ መገልገያዎች 20,000.00 /ሃያ ሺህ/ ብር፣ ለደንብ ልብስ 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ/ ለፅዳት እቃዎች 20,000.00 /ሃያ ሺህ/ ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ብቻ ለጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  5. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃዎች ድምር ዋጋ 10% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ ወይም በካሽ ብቻ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከተቋሙ ጋር ህጋዊ ውል ይፈራረማሉ
  6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቹን በሎት የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መግዛት አለባቸው።
  7. ተጫራቾች መረጃዎቻቸውን ማለትም ፋይናንሺያል ኦሪጅናል፣ ፋይናንሺያል ኮፒ፣ ቴክኒካል ኦሪጅናል እንዲሁም ቴክኒካል ኮፒ በማዘጋጀትና ለየብቻ 4/አራት ፖስታ በማሸግ እና የጨረታ ሰነዱ እያንዳንዱ ገፅ ላይ የድርጅቱ ማህተም ተደርጎ ጋዜጣው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በሚቆጠር የስራ ቀናት እስከ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 0400 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን ስርዝ ድልዝና ፍሉድ ተቀባይነት የለውም።
  8. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር የስራ ቀን 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ 430 በቂርቆስ ማኑፋክቸሪንግኮሌጅ ቅጥር ግቢ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታ መክፈት ስርአቱ አይስተጓጎልም።
  9. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ

  • አድራሻ፡ከቂርቆስ ቤተክርስቲያን ወደ ቄራ በሚወስደው አዲሱ መንገድ ከቴሌ 200 ሜትር ወረድ ብሎ አርባ ምንጭ አሳ ቤት አካባቢ የቀድሞ ስሙ ዕውቀት አምባ ከፍ//////ተቋም ግቢ።
  • ስልክ ቁጥር 011-470-5249 ወይም 011-416-8823

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ እና ክህሎት ቢሮ የቂርቆስ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ