በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 26, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2018

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ሚሽን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች፡-

  1. 1 ደንብ ልብስ የሴትና የወንድ ቆዳ ጫማ ፣የወንድና የሴት የሰነድ መያዣ ቦርሳ የመሳሰሉት፤
    • ሎት 2 አላቂ የጽህፈትና የቢሮ ዕቃዎች እና ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ክላሰር 250 ግራም፣ የፕሪንተርና የፎቶ ኮፒ ቀለም የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ፣ ፍላሽ፣ ሳይንትፊክ ካልኩሌተር የመሳሰሉት፤
    • ሎት 3 የፅዳት ዕቃዎች ኤርፍሬሽነር፣ ፍሊት፣ ሳኒታይዘር፤ የመሳሰሉት፣
    • ሎት፤-4 ኤሌክትሮኒክስና ቋሚ ዕቃዎች ኤልሲዲ ሞኒተር፤ ፕሮጀክተር ኢንዲኬተር ፖይንተር ፕሮጀክተር የውሃ ማጣሪያ፣ የመሳሰሉት፣
    • ሎት 5 ፈርኒቸር፣
    • ሎት 6 የመኪና ጌጣ ጌጥ፤ የመኪና ልብስ፤ የመሳሰሉት፣
    • ሎት 7 ህትመት የተለያዩ ብሮሸሮች፤ የኮሚሽኑ ብራንድ ወይም ሎጎ ያለበት (ጃንጥላ፤ እስክሪብቶ፤ ማስታወሻ ደብተር፣ ሸራ ቦርሳ) እና
    • 10 የተለያዩ ፕሮጀክት ጽሁፎች በአማርኛ እና በእንግሊዘኛተጫራቾች በዘርፉ የተሰማራችሁ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ፣ የቫት የምዝገባ ሰርተፍኬት፣ እና ሌሎች ለጨረታ መወዳደር አስፈላጊ የሆኑ ማስረጃዎች ማቅረብ አለባችሁ።
  2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ሎት 1 የደንብ ልብስ ብር 3,000 ሎት 2 አላቂ የጽህፈትና የቢሮ ዕቃዎች እና ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ብር 5,000 ሎት 3 የፅዳት ዕቃዎች 5,000 ሎት 4 ኤሌክትሮኒክስ ቋሚ ዕቃዎች 5,000 ሎት 5 ፈርኒቸር 5,000 ሎት 6 የመኪና ጌጣ ጌጥ ብር 5,000 ሎት 7 – ለህትመት ብር 5,000 ለፕሮጀክት ብር 15,000 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ስም በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ብቻ በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መመሪያ የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋት 400 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ) ብቻ በመክፈል አድ በግዢ፤ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት 8 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 802 ማግኘት ይችላሉ፤
  4.  ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸው በመግለጽ በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ድረስ ኮሚሽኑ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በግዢ፣ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት 8 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 802 ማስገባት ይጠበቅባቸዋል ጨረታው 11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 430 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤
  5. ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
  6. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይናንሻል (የመወዳደሪያ ዋጋ የተሞላበት ሰነድ) ኦርጅናል እና ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል ዶክመንቶችን (የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ኦርጅናልና የተጠየቁ አስፈላጊ የንግድ ፍቃዶችና መረጃዎች ኮፒ) በፖስታ ውስጥ በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት አለባቸው፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ተካፋይ ሆኖ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የተሰጠውን ዋጋ ለማሻሻል፣ ለመለወጥ ወይም ትቼዋለው ማለት አይችልም፤
  8.  ማንኛውም ተጫራች ማጭበርበር ወይንም ሙስናን በተመለከተ በኢትዮጵያ ህጎች የተደነገገውን የሚያከብር መሆን ይገባዋል፤
  9. ጨረታውን ለማዛባት ሙከራ የሚያደርግ ተጫራች ከጨረታው እንደሚሰረዝ እና ወደፊትም እንዳይሳተፍ እንደሚታገድ እንዲሁም ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና እንደሚወረስበት ማወቅ ይኖርበታል፤
  10. ተጫራቾች ለምታቀርቧቸው ናሙናዎች የምታመጡበት ዕቃዎች ጠንካራ እና በቀላሉ ሊቀደዱ የማይችሉ መሆን አለባቸው!

አድራሻ፦ ልደታ ክፍለ ከተማ ሜክሲኮ ዮቤክ ህንፃ 8 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 802 በግዢ፤ ንብረት 802 አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት

ለበለጠ መረጃ በስ..011-5-57-78-46 እና 0913-04-5738 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ኮሚሽን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *