Your cart is currently empty!
አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውን አክስዮኖች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Reporter(Oct 26, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
በድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውንና በሠንጠረዡ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4 (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።
- ተበዳሪው /መያዣ ሰጪው/ በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ። ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል።
- የጨረታ ቦታ አዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ለገሀር በሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት 4ኛ ፎቅ ፎርክሎዠር እና ዴት ሊትጌሽን ለጨረታ ባዘጋጀዉ ቢሮ ዉስጥ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115 15 11 53 እና 0115 15 07 አ.አ በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
|
የተበዳሪዉ ስም |
የንብረቱ አይነት እና አገልግሎት |
የአክስዮን ሰርቲፊኬት ቁጥር |
የጠቅላላ አክስዮኖች ብዛት ቁጥር |
የአንድ አክስዮን ዋጋ በብር |
የአክስዮኑ ዋጋ በብር |
የጠቅላላ አክስዮኖች የጨረታ መነሻ ዋጋ በብር |
ጨረታው የሚካሄድበት ቀን |
የምዝገባ ሰዓት |
የጨረታ ሰዓት |
መግለጫ |
|
ፍኖት የጤና አገልግሎት አክስዮን ማህበር |
የወጋገን ባንክ አ.ማ አክስዮኖች |
6868 |
323 |
1000 |
323,000 |
2,000,000.00 |
ህዳር 03 ቀን 2018 ዓ.ም |
8፡30-9፡30 |
9፡30-10፡00 |
አክስዮኖቹ ተነጣጥለዉ አይሸጡም |
|
0607 |
1000 |
1000 |
1,000,00 |
|||||||
|
2770 |
232 |
1000 |
232,000 |
|||||||
|
4709 |
308 |
1000 |
308,000 |
|||||||
|
4405 |
137 |
1000 |
137,000 |
|||||||
|
ጠቅላላ ድምር |
2000 |
|
2,000,000.00 |