ሕብረት ባንክ አ.ማ. ለሰጣቸው ብድሮች በመያዣነት የያዛቸውን ንብረቶች በግልፅ ሐራጅ(ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል


Reporter(Oct 26, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የሐራጅ ማስታወቂያ፤

ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቅርንጫፎቹ በኩል ለሰጣቸው ብድሮች በመያዣነት የያዛቸውንና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልፅ ሐራጅ(ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል።

ተራ .

የተበዳሪ ስም

የአስያዥ ስም

አበዳሪው ቅርንጫፍ

ቤቶቹ የሚገኙበት አድራሻና የቦታ ስፋት

የይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ቁጥር

የሐራጅ መነሻ ዋጋ በብር

ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት

1

ሃልካያን ኢንዱስትሪ እና ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግ//

ሃልካያን ኢንዱስትሪ እና ትሬዲንግ ኃላ/የተ/ የግ//

ሸገር

አዲስ አበባ ከተማ፣አራዳ /ከተማ፣ወረዳ 09 የቦታ ስፋት 852.6 .ሜ፣አገልግሎቱ ለድርጅት የሆነ በግንባታ ላይ ያለ ሕንፃ፤

 

/ሊዝ/17/08/6362/01

 

355,897,544.00

ኅዳር 30 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 500 እስከ 600 ሰዓት

2

አቶ ተሰማ አያኖ ሻመና

አቶ ተሰማ አያኖ ሻመና

ለቡ ላፍቶ

አዲስ አበባ፤ንፍስ ስልክ ላፍቶ /ከተማ፣ወረዳ 01፤የቦታ ስፋት 175 .ሜ፣አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ ቤት

AA000080112118

20,346,579.00

ታህሳስ 01 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 5:00 እስከ 6:00 ሰዓት

3

አቶ ጁሀር ሰይድ እንድሪስ

አቶ ጁሀር ሰይድ እንድሪስ

ጎላ ሰፈር

አዲስ አበባ፣ቦሌ /ከተማ ወረዳ 10፣የቦታ ስፋት 48.87 .ሜ፣ አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ ኮንዶሚኒየም ቤት

AA0000610074942590115

2,632,133.00

ታህሳስ 02 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 5:00 እስከ 6:00 ሰዓት

4

አቶ አበራ ገብሬ ብርሃኑ

አቶ አበራ ገብሬ ብርሃኑ

ወልድያ

ሰሜን ወሎ ዞን፣ወልድያ ከተማ፣ቀበሌ 03 የቦታ ስፋት 150 .ሜ፣አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ  ቤት

////9148/14

1,688,620.00

ታህሳስ 03 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 5:00 እስከ 6:00 ሰዓት

5

አቶ ረሻድ አህመድ በሽር

አቶ ኑርሰፋ ኢብራሂም

ወልቂጤ

ወልቂጤ ከተማ፣ጉብሬ /ከተማ፣ቀበሌ 01 የቦታ ስፋት 250 .ሜ፣አገልግሎቱ ለንግድ የሚውል ቤት፣

/ 242

1,747,345.00

ታህሳስ 03 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 500 እስከ 600 ሰዓት

6

አቶ መኳንንት ታደሰ ረዳ

አቶ መኳንንት ታደሰ ረዳ

ባህርዳር

ባህርዳር ከተማ፣አፄ ቴዎድሮስ /ከተማ፣የቦታ  ስፋት 728 .ሜ፣አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ ቤት

31012/07

18,035,600.00

ታህሳስ 08 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 500 እስከ 600 ሰዓት

የሐራጅ ደንቦች፡-

1. ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በሕብረት ባንክ አ.ማ.(Hibret Bank S.C) ስም የተሰራ የባንክ ክፍያ ማዘዣ(ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡ከባንክ ክፍያ ማዘዣ(ሲ.ፒ.ኦ) ውጭ የሚቀርብ የጨረታ ማስያዣ ተቀባይነት የለውም።

2. ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከባንኩ የሕግ አገልግሎቶች መምሪያ ወይም ከቅርንጫፉ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ዕለት ሶስት ቀናት አስቀድሞ መጎብኘት ይችላል።

3. ከተራ ቁጥር 1- 3 የተጠቀሱት ንብረቶች ሐራጅ የሚካሄደው የሕብረት ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ(ሕብር ታወር) 26ኛ ፎቅ የሕግ አገልግሎት መምሪያ ባለው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ነው፡፡በተራ ቁጥር 4-5 ላይ የተጠቀሱት ንብረቶች ሐራጅ ደግሞ ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ ላይ ይካሄዳል፡፡በተራ ቁጥር 6 ላይ የተጠቀሰው ንብረት ሐራጅ ደግሞ ባህርዳር ከተማ፣ዳግማዊ ምኒልክ ክ/ከተማ፣ቀበሌ 14 የተባበሩት ማደያ ፊት ለፊት በሚገኘው የባንኩ ሰሜን ምዕራብ ቀጠና(ዲስትሪክት) ቢሮ ውስጥ ይካሄዳል።

4. በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ተበዳሪ እና አስያዥ ብቻ ናቸው፡፡ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል፡፡ተጫራቾች የሕግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ሕጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ሰው ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ፅ/ቤት ወይም በተመሳሳይ አካል የፀደቀ መመስረቻ ፅሁፍ(የመተዳደሪያ ደንብ)፣ቃለ ጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት።

5. የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይደረጋል።

6. ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡ከፍተኛ ዋጋ ለሰጠ ተጫራች ደግሞ ያቀረበውን ዋጋ ባንኩ ሲቀበለው ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ እንዲከፍል የሚገልፅ ደብዳቤ የሚሰጠው ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል፡፡በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል።

7. የጨረታው አሸናፊ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች የጨረታ አሸናፊ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን ይከፍላል።

8. ባንኩ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

9.  ለተጨማሪ መረጃ ፡ በስልክ ቁጥር፡ ሸገር ቅርንጫፍ ፡ 011 1 26 54 62፣ለቡ ላፍቶ ቅርንጫፍ 0114 19 90 61፣ጎላ ሰፈር ቅርንጫፍ፡ 0111 26 22 07፣ወልድያ ቅርንጫፍ ፡ 0333 31 20 21/20 ፣ ወልቂጤ ቅርንጫፍ፡ 0113 65 85 27 ወይም የሕግ አገልግሎቶች መምሪያ  0114 70 03 15/47 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *