Your cart is currently empty!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአድዋ ድል መታሰቢያ የተለያዩ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎችን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት በሚቆይ ውል በኪራይ ማሰራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 28, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአድዋ ድል መታሰቢያ በጨረታ መለያ ቁጥር፡- አ/ድ/መ/ 002/2018 ለ2018 በጀት አመት የሚያስፈልጉትን የተለያዩ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎችን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት በሚቆይ ውል በኪራይ ማሰራት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ ፈቃደኛ የሆናችሁ ተጫራቾች እንድትሳተፉ እየጋበዝን የተሽከርካሪዎቹን ዝርዝር ዓይነት ከታች ባለው ሰንጠረዥ ተመላክቷል።
| ምድብ ቁጥር | የሚገዙ እቃዎች አይነት 
 | ብዛት 
 | ሞዴል | የጨረታ ማስከበሪያ ብር 
 | 
| ሎት 1 
 | suv ተሽከርካሪ–V6 twine turbo | 1 | 2015/2023 እና በላይ | 100,000 ብር 
 | 
| Suv ተሽከርካሪ | 2 | 2015/2023 እና በላይ | ||
| Sedan አውቶሞቢል | 1 | 2013/2020 እና በላይ | ||
| Minibus ተሽከርካሪ | 1 | 2013/2020 እና በላይ | 
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /AI/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በአድዋ ድል መታሰቢያ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተው አካውንት ቁጥር 1000613546867 በመከፈል ደረሰኝ /ስሊፕ/ ይዞ በመቅረብ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ይሆናል።
- የጨረታው ሰነድ መመለሻ የመጨረሻ ቀን 29/02/2018 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ነው።
- ጨረታው በቀን 29/02/2018 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት ማለትም በቀን 29/02/2018 ዓ.ም በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ሌሎች መረጃዎችን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታ ሰነዱ ፒያሳ አራዳ ህንጻ ፊት ለፊት አድዋ ድል መታሰቢያ አስተዳደር ቢሮ ሌቭል – 2 ፋይናንስ ክፍል ይገኛል።
- አድራሻ፡- ፒያሳ አራዳ ህንጻ ፊት ለፊት አድዋ ድል መታሰቢያ አስተዳደር ቢሮ ፋይናንስ ክፍል
- ስልክ ቁጥር፡- +251-09-90-45-12-00
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አድዋ ድል መታሰቢያ