Your cart is currently empty!
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የኢትዮ-ጃፓን ህዳሴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የደንብ ልብስ፣ አላቂ የጽዳት እቃ፣ የስፖርት ትጥቆች፣ አላቂ የህክምና እቃዎች፣ የትም/እቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 27, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የኢትዮ–ጃፓን ህዳሴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የደንብ ልብስ፣ አላቂ የጽዳት እቃ፣ የስፖርት ትጥቆች ፣ አላቂ የህክምና እቃዎች፣ የትም/እቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡–
1. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና የምስክር ወረቀት ያላቸው።
ተጫራቾች ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ ቲን ነምበር ያላቸውና ቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች የእቃውን ናሙና ከዓይነቱ አንድ አንድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታው ውጤት ከታወቀ በኋላ ያቀረቡት ናሙናዎች የተሸናፊ ሲመለስ የአሸናፊ ተጫራቾች ናሙና ዕቃው እስከሚያቀርቡ ድረስ አይመለስም።
3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ/ብር በመክፈል ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ኢጃ/ሀ/2ኛ/ደ/ት/ቤት የፋይናንስና ግዢ ንብረት አስተ/ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ መቻል አለባቸው።
5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና / 1. ሎት (lot) 1. (1500000 ብር)፣ 2. ሎት 2(lot) (ብር 900,000)፣ 3. ሎት 4 (lot) (ብር 60000)፣ 4. ሎት (lot)5 (ብር 1061000)፣ 5. ሎት(lot) 7 (ብር 1400000 )፣ 6. ሎት (lot) 8 (ብር 727442)፣ 7. ሎት 4 (lot)13 (ብር 158232)፣ 8. ሎት (lot) 22 (ብር 1700000 ) በጥቅል ብር ሁለት ፐርሰንት ብር በባንክ በተመሰከረለት የክፍያ ትዕዛዝ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናልና ኮፒውን የጨረታ ቁጥር እና የዕቃውን ዓይነት በግልጽ ኤንቨሎፕ ላይ መጻፍ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ኢ/ጃ/ሀ/2ኛ ደ/ት/ቤት የፋይናንስና ግዢ ንብረት አስተ/ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 3 ማስገባት አለባቸው።
7. ጨረታው በጋዜጣ በወጣበት በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በአ/አበባ ከተማ አስተዳደር ኢ/ጃ/ሀ/2ኛ/ደ/ት/ቤት ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
8. ተጫራቾች በጨረታው ሠነድ ላይ የተዘረዘሩትን ጥሬ ዕቃዎች የእያንዳንዱን ነጠላ ዎጋ መጥቀስ ይኖርባቸዋል።
9. ተቋሙ ጨረታውን ለመገምገም የሚጠቀምባቸው መስፈርቶች ዕቃዎች መስሪያ ቤቱ ባስቀመጠው specification መሆናቸው ጥራት ዋስትና አጠቃሎ ማቅረብ ግምት ውስጥ ይገባል።
10. ተቋሙ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
11. የጥቃቅነንና አነስተኛ የሆኑ ተጫራቾችአምራች እና በሀገር ውስጥ ምርት መወዳደር ይችላሉ።
12. ሌሎች ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
13. ማንኛውም ተጫራቾች በሳምፕሉ ላይ የራሱን ስም (የድርጅቱን ማህተም)የመሳሰሉትን የጻፈ(ማህተም ያደረገ)ከውድድሩ ይሰረዛል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 011 434 6843/6914
ፖስታ ሣጥን ቁጥር 540
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የኢትዮ–ጃፓን ህዳሴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት