በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጽዳት እቃዎች፣ ልዩልዩ እቃዎች፣ ስፔርፓርት እቃዎች፣ ኮስሞቲክስ ዕቃዎች እና አልባሳት እቃዎች ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 27, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 06/2018

በኢ... ጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ጉምሩክ //ቤት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ የጽዳት እቃዎች ልዩልዩ እቃዎች፣ ስፔርፓርት እቃዎች፣ ኮስሞቲክስ ዕቃዎች እና አልባሳት እቃዎች በሐራጅ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ . 06/2018 . እቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም፡ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሱ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

1. በጨረታው ሽያጭ ስርዓት ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የጸና የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ለሀራጅ ጨረታ በጨረታ መክፈቻ ቀን ይዘው መቅረብ አለባቸው።

2. ከላይ በተራ ቁጥር አንድ የተገለጸው ቢኖርም ግምታዊ ዋጋው ከብር 500 ሺህ በታች የሆነ ማንኛውም እቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም እንዲሁም የሚሸጠው እቃ ተሽከርካሪ ሲሆን የተሽከርካሪው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተስብ ከሆነ ሰው በስተቀር ማንኛውም እድሜው 18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ቅድመሁኔታዎቹን ማሟላት ሳያስፈልገው በጨረታው ሊሳተፍ ይችላል።

3. በሐራጅ ጨረታ ለወጡት እቃዎች ለመሳተፍ ለአልባሳት ዘርፍ እቃዎች 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) ለልዩ ልዩ ዘርፍ እቃዎች 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) ለጽዳት ዘርፍ ዕቃዎች እቃዎች 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) ለእስፔር ፓርት ዘርፍ እቃዎች 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) እና ለኮስሞቲክስ ዘርፍ እቃዎች 200,000 (ሁለት መቶ ብር) ለየብቻው የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ (CPO) በቀጥታ አካውንት ቁጥር 1000296553216 በጋላፊ ጉምሩክ ቅርንጫፍ /ቤት ስም በማሠራት የጨረታ ሰነዱን እና በተራ ቁጥር አንድ የተገለጹትን መረጃዎች በመያዝ 22/02/2018 . ከጠዋቱ 350 ላይ መገኘት አለባቸው።

4. ከላይ በተራ ቁጥር 3 በተገለጸው መሰረት በቂ የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ተጫራች መወዳደር ወይም መጫረት አይችልም።

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት 200-33 ሰዓት የእቃዎቹን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 10000 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 22/02/2018 ጠዋት 330 ድረስ በውርስ መጋዘን አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 08 መግዛት ይችላሉ።

6. ለጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎች ለናሙና ዕይታ የሚቀርቡበት ጊዜ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ከጥቅምት 17 ቀን 2018 . ጀምሮ እስከ ጥቅምት 22 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 330 ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ 200-330 ሰዓት የእቃዎቹን ዝርዝር መመልከት ይችላሉ።

7. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ የጊዜ ሰሌዳ (ስኬጃል) መሠረት መጫረት ይችላሉ።

.

የቅ//ቤቱ ስም

የጨረታው አይነት

የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ

የጨረታው መዝጊያ  እና መክፈቻ ቀንና

1

ጋላፊ ጉምሩክ //ቤት

ሐራጅ ጨረታ

እስከ 22/02/2018 ከጠዋቱ 330 ድረስ

22/02/2018 .350 ሰዓት ይከፈታል

የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡በጋላፊ ///ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል። ተጫራቾች በተራ ቁጥር አንድ የተጠቀሱ ማስረጃዎች ኦርጂናል ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡

8. ምድብ ለወጣላቸው ሐራጅ እቃዎች ጨረታው የሚካሄደው በምድብ ሲሆን ተጫራቾች አሸናፊ የሚያደርጋቸው ለምድቡ ባቀረቡት የአጠቃላይ እቃዎች ከፍተኛ ዋጋ ይሆናል።

9. ተጫራቾች ከአሸነፉበት የእቃ ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) የሚጨመር ይሆናል።

10. ተጫራቾች ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በተመለከተ ለአሸናፊው ተጫራች ካሸነፉት የዕቃ ዋጋ ላይ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ውጤቱ በተገለጸ 3 (ሶስት) ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

11. አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ የመረከብ እና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይችላል።

12. አሸናፊ ተጫራች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ 05 (በአምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን እቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ያለበት ሲሆን ይህን ባይፈጽም ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ የሚቀርብ ሲሆን ነገር ግን አሸናፊው የአሸነፈበትን የእቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ እቃውን ያላነሳ እንደሆነ ለሚቆይበት ተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ የሚከፍል ይሆናል። ሆኖም እቃውን በሁለት ወር ውስጥ ካላወጣ ለንብረቱ የተከፈለው ዋጋ ለመስሪያቤቱ ገቢ ሆኖ እቃው እንደተተወ ተቆጥሮ በሽያጭ ይወገዳል።

13. በጨረታ የሚሸጠው እቃ በቅርንጫፍ /ቤቱ ከመወረሱ በፊት የእቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም።

14. ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ ውርስ መጋዘን አስተዳደር የሥራ ሂደት ስልክ ቁጥር 033-559-0114 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት