Your cart is currently empty!
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 የአቃቂ መ/የመ/ደ/ት/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ የደንብ ልብስ፣ አላቂ የት/ት እስቴሽነሪ ዕቃዎች፣ የላብራቶሪ ዕቃዎች፣ አላቂ የጽዳት ዕቃዎች እንዲሁም ልዩ ልዩ መሳሪያዎች መጽሀፍትን ጨምሮ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 27, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 002/2018
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 የአቃቂ መ/የመ/ደ/ት/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ የደንብ ልብስ፣ አላቂ የት/ት እስቴሽነሪ ዕቃዎች፣ የላብራቶሪ ዕቃዎች፣ አላቂ የጽዳት ዕቃዎች እንዲሁም ልዩ ልዩ መሳሪያዎች መጽሀፍትን ጨምሮ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለፈለገ ነዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል።
|
የ ሎት. ቁ |
የሎት ዝርዝር |
CPO መጠን |
|
የሎት 1 |
የደንብ ልብስ |
30,789.00 |
|
የሎት 2 |
አላቂ የት/ት እና እስቴሽነሪ |
30,364.00 |
|
የሎት 3 |
የላብራቶሪ ዕቃዎች |
13,780.00 |
|
የሎት 4 |
አላቂ የጽዳት ዕቃዎች |
27,794.00 |
|
የሎት 5 |
ልዩ ልዩ መሳሪያዎች |
4,694.00 |
|
የሎት 6 |
ቋሚ ዕቃዎች |
5,000.00 |
|
የሎት 7 |
ህትመት |
947.00 |
በጨረታው ለመሣተፍ የሚያስፈልጉ
1. የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ በመንግስት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው።
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
3. የአቅራቢዎች የምዘገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው።
4. ተጫራቹ በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው መሆን አለባቸው።
5. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ በሎቱ ፊት ለፊት የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን በአቃቂ መንግስት የመ/ደ/ት/ቤት ስም በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ(CPO) ለእያንዳንዱ ለሚሳተፉበት ሎት ማስያዝ ግዴታ አለበት።
6. የጨረታው ጊዜ ጸንቶ የሚቆየው ለ60 ቀን ብቻ ነው።
7. ተጫራቾች ዘወትር በስራ ሰዓት ከት/ቤቱ የፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 03 የጨረታ ሰነዱን በየሎቱ የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/በመክፈል መውሰድ ትችላላችሁ።
8. በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ተጫራቾች ለሚያመርቱት ምርት ብቻ ከክፍያ ነፃ ካደራጃቸው አካል ደብዳቤ በማጻፍ እና ለሚያመርቱት ምርት/ዕቃ/ እንደማንኛውም ተጫራች ሰነዱን በመግዛት እና በየሎቱ የተቀመጠውን የጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ ጨረታውን መሳተፍ ይችላሉ።
9. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ዕቃውን በራሳቸው ትራንስፖርት በማጓጓዝ መስሪያ ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማስገባት እና ማስረከብ አለባቸው።
10. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የዕቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
11. ተጫራቾች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በጨረታ ሰነዶችን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን ከማስረጃው ጋር በማደራጀት በታሸገ ፖስታ ት/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
12. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ11ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ በዚያው እለት በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ ሂሳብ ክፍል ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 11ኛው ቀን በዓል ወይም እረፍት የሚሆን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን የሚከፈት ይሆናል።
13. ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።
14. አሸናፊ ተጫራቾች አሸናፊነቱ እንደተገለጸለት የውል ማስከበሪያ 10% ሲፒኦ ዋስትና ማስያዝ ግዴታ አለባቸው።
15. ተጫራቾች ባሸነፉበት የዕቃዎች ብዛት ላይ መስሪያ ቤቱ 20% ወደ ላይ 20% ወደታች አድርጎ መግዛት ይችላል። እንዲሁም ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡- አቃቂ ንግድ ባንክ 100 ሜትር አለፍ ብሎ በስተቀኝ በኩል ይገኛል።
ስልክ 011 471 5756
ማሳሰቢያ፡-
በት/ቤቱ ሂሳብ ቁጥር 1000014607537 የሚገዙበትን የጨረታ ስነድ ሂሳብ የተወዳዳሪው ድርጅቱን ስም በመጥቀስ አቃቂ መንግስት የመ/ደ/ት/ቤት ገቢ በማድረግ የባንክ ሲልፕ ይዛችሁ በመምጣት ሰነዱን መውሰድ ትችላላችሁ።
አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 አቃቂ መንግስት የመ/ደ/ት/ቤት