Your cart is currently empty!
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለሥልጣን የሆሣዕና ዲስትሪክት ጽ/ቤት በሥሩ ለሚገነባቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና ፕሮጀክቶች ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ የሰርቪስ አይሱዚ መኪናዎች እና የውሃ ቦቴዎችን ብቁ አቅራቢዎችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 27, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ሆሣዕና ዲስትሪክት 001/2018
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለሥልጣን የሆሣዕና ዲስትሪክት ጽ/ቤት በሥሩ ለሚገነባቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና ፕሮጀክቶች ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ የሰርቪስ አይሱዚ መኪናዎች እና የውሃ ቦቴዎችን ብቁ አቅራቢዎችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
በመሆኑም፡–
1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችለውን የ2018 የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የንግድ ሥራ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተከፈለበት የምዝገባ ምስከር ወረቀት እና በኮንስትራክሽን መሣሪያዎች አቅራቢነት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ/ብር በመክፈል ከፋይናንስና ሎጅስቲክስ ስራ ሂደት ቢሮ መውሰድ ይቻላል።
3. ተጫራቾች ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ የፋይናንሻል ፕሮፖዛሉን በተለያየ ፖስታ በማድረግ አንድ ዋና እና አንድ ኮፒ ‹‹ኦርጅናል›› እና ‹‹ኮፒ›› በማያያዝ እና የጨረታ ማስከበሪያውንም በባንኮች የተረጋገጠ ሲፒኦ በተለያየ ፖስታ ለብቻው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሠረት ሲሆን ጨረታው ዜግነት ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው።
5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ማቅረቢያና ተያያዥ ዶክመንቶችን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ሆሣዕና ዲስትሪክት ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ አስራ አምስተኛው የስራ ቀን ከቀኑ 11፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸው። ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም።
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋ 1% በባንኮች በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
7. ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ቢድ ቦንድ ለተሸናፊዎች ወዲያውኑ የሚመለስ ይሆናል::
8. አሸናፊው በጨረታ ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ እስከ አምስተኛ ቀን ውል መግባት ይኖርበታል። በተሰጠው ጊዜ ገደብ ውስጥ ውል የማይገባ ከሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
9. ዲስትሪክቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
10. ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ።
የስልክ ቁጥር 046-555-2347፣ 046-555-2348፣ 046-555-2349
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለሥልጣን የሆሣዕና ዲስትሪክት ጽ/ቤት