Your cart is currently empty!
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የወራቤ ዲስትሪክት ጽ/ቤት በስሩ ላሉ ፕሮጀክቶች ለሰርቪስ እና ለሌሎች አገልግሎቶች የሚውል አይሱዙ፣ የውሃ ቦቴ እና ሚኒባስ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 28, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የወራቤ ዲስትሪክት ጽ/ቤት በስሩ ላሉ ፕሮጀክቶች ለሰርቪስ እና ለሌሎች አገልግሎ የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡
- ማለትም፡– አይሱዙ ፣ የውሃ ቦቴ እና ሚኒባስ
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችለውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት የተዛመደ የንግድ ስራ ወይም የአገልግሎት ስራ ፍቃድ፣ በዘርፉ ለሚመለከተው አካል ፈቃድ የተሰጠ እና በአቅራቢነት ዝርዝር ውስፕ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ የፋይናንሽያል ፕሮፖዛል ፖስታ ላይ በማድረግ አንድ ዋና እና 1 ኮፒ ኦርጅናል” እና “ኮፒ በማለት እና የጨረታ ማስከበሪያውንም በተለየ ፖስታ ለብቻው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱን የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከዲስትሪክቱ ቢሮ ቁጥር 5 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሠረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው፡፡
- አቅራቢዎች በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉት ይህን ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን ከቀኑ 6፡00 ድረስ ይሆናል፡፡ ጨረታው በዚያኑ ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡ እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጠቅላላ ዋጋ 1.5 ፐርሰንት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPO (በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም::
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሠረት ጨረታውን ማቅረብ አለባቸው:: ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውንም ተጫራች ተቀባይነት የለውም፡፡
- ዲስትሪክቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡
ስልክ ቁጥር/0467710428/423/421/0916692830/0938072795/
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የወራቤ ዲስትሪክት ጽ/ቤት