Your cart is currently empty!
በአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሌጅ በ2018 በጀት ዓመት የባህር ዛፍ ማገዶ እንጨት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 29, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር AAPPC 002/18
በአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሌጅ በ2018 በጀት ዓመት በአመቱ በተለያዩ ወቅት ለሚሰጣቸው ልዩ ልዩ ስልጠናዎች ለሰልጣኞች አገልግሎት የሚውሉ፦
- ሎት 1 የባህር ዛፍ ማገዶ እንጨት ግዥ በማስፈለጉ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤
በመሆኑም በዚሁ ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች
- ጨረታው የሚከናወነው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግዥ አዋጅ በተገለፀው ግልፅ ጨረታ ስነ-ስርዓት መሰረት ይፈጸማል የባህር ዛፍ ማገዶ እንጨት ጨረታው የሚያከናውነው ብቁ ከሆኑ ተጫራቾች እና ከስራው ጋር አግባብነት ያለው ሆኖ በ2018 ዓ/ም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያለው፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚገልፅ ወቅታዊ ደብዳቤ/Tax clearance ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ከገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር እንዲሁም ተ.እ.ታ /VAT/ ሰርተፊኬት እና ቲን /TIN/ ሰርተፊኬት ኮፒውን ማቅረብ የሚችል ይሆናል፤ በሁሉም ሎቶች ላይ የሚወዳደሩ አቅራቢዎች የሚያቀርቡት ሰነድ በአጠቃላይ የታደሰ መሆን አለበት።
- ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት የኢትዮጵያ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ከፍለው የጨረታውን ሰነድ ቢሮ ቁጥር 28 በስራ ቀናት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ። በአነስተኛ እና ጥቃቅን ተቋማት አዋጅ መሰረት የተቋቋሙ ተቋማት ለጨረታው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በአነስተኛ እና ጥቃቅን ተቋማት የተቋቋሙበት የህጋዊነት ማስረጃ በማሳየት ያለ ክፍያ በነፃ ይሰጣቸዋል። ከአደራጃቸው አካል በሚጫረቱበት ሎት በዘርፉ መሰማራታቸውን የሚገልፅ የቅርብ ጊዜ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች በሎት 1 ብር 15,000.00 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠለት ሲ.ፒ.ኦ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሌጅ ስም አዘጋጅቶ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ 10 ቀናት ቅዳሜ፤ እሁድን እንዲሁም የበዓል ቀናትን ጨምሮ በኮሌጁ ፋይናንስና ግዥ ዲቪዚዮን በመቅረብ ለዚህ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በአንድ ኤንቨሎፕ /ፖስታ ፋይናንሺያል እና ቴክኒካል ኦሪጂናል እና ኮፒ በድምሩ በ2 ፖስታ ሰነዶችን በመለየት ማስገባት አለባቸው።
- ዘግይተው የቀረቡ የጨረታ መልሶች ተቀባይነት የላቸውም፤ የጨረታው ሳጥን በ11ኛው ቀን በ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያኑ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ አዳራሽ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ሲሆን ይከፈታል። የመዝጊያውና የመክፈቻው ቀን የመንግሥት ስራ ቀን ወይም ካላንደር /የቀን መቁጠሪያ/ የሚዘጋው በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ስራ ቀን ይሆናል፡።
- ሌሎች ደጋፊ ሰነዶችን እንደ የመልካም ስራ አፈፃፀም እና የመሳሰሉትን ማቅረብ የተሻለ ውጤት አለው።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ኮልፌ ሉኳንዳ አዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሌጅ ማሰልጠኛ ማዕከል የቀድሞ ፈጥኖ ደራሽ ግቢ/ አጠገብ።
ለበለጠ መረጃ 0112-73 94-86 ፤ 0112-73-95-48 ወይም 251-118-33-38-45
በአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሌጅ