Your cart is currently empty!
የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ለመኖሪያ፣ ለንግድ፣ ለማህበራዊ አገልግሎት/ የሚውሉ ቦታዎችን በግልፅ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 29, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የ23ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
- የጨረታ ዙር፡– 23ኛ
- የጨረታው አይነት፡– መደበኛ
- የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ጫጫን ጨምሮ በሁሉም ክ/ከተሞች የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 እና ይህንኑ አዋጅ ለማስፈፀም የአብክመ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ ባወጣው ደንብ ቁጥር 103/2004 በክፍል 3 በአንቀፅ 10 በንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ከ”ሆ” እስከ “ሠ” በተዘረዘረው መሰረት ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች ማለትም ለመኖሪያ፣ ለንግድ፣ ለማህበራዊ አገልግሎት/የሚውሉ ቦታዎችን በግልፅ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል። በመሆኑም መጫረት የሚፈልግ ሰው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 1,000/ አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 10 ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው መሰረት መሆን ይኖርበታል።
- ተጫራቾች ሁለት የተለያዩ ተመሳሳይ ፖስታዎችን በማዘጋጀት 1ኛ ክፍል ሁለት የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን እና ከፍል ሶስት የጨረታ ሀሳብ ማቅረቢያ ሰነዱን 2ኛ ሲፒኦን ሁለቱን ሰነዶች አንዳንድ ኮፒ በማድረግ ኦሪጅናሉን ለብቻ ኮፒውን ለብቻ በተለያዩ ፖስታዎች በማሸግና በፖስታዎቹ ላይ ኦሪጅናልወይም ኮፒ በማለት ለይቶ በመፃፍ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ፖስታውን እስከ 10ኛው (አስረኛው) ቀን 11፡00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 7 ኦሪጅናሉን ሰነድ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ኮፒውን ሰነድ ደግሞ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው የሚዘጋው የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ተከታታይ የስራ ቀን በ11፡00 ሰዓት ላይ ይሆናል።
- ቦታውን መጐብኘት ለሚፈልግ ተጫራች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገለፀው መርሃ ግብር መሰረት የምናስጎበኝ ይሆናል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው አዳራሽ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።
- የጨረታ መከፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በጨረታ ሰነዱ ላይ እና በመምሪያው ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ እንዲሁም በዌብ ሳይት WWW.mudc.Gov.et ማግኘት ይችላሉ።
- መስሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ