Your cart is currently empty!
አቢሲንያ ባንክ አ.ማ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውን ንብረት በሚገኙበት ቦታና ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Reporter(Jan 25, 2026)
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ
አቢሲንያ ባንክ አ.ማ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውንና ከዚህ በታች ባለው ሰንጠረዥ የተመላከተውን የማይንቀሳቀስ የመያዣ ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/1990 እንደተሻሻለው ለባንኮች በተሰጠው ስልጣን መሠረት ንብረቱ በሚገኙበት ቦታና ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
ተጫራቾች ለጨረታው ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4 (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ አ.ማ. ስም ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ::
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል:: በእነዚህ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል:: በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ. በዕለቱ ይመለስላቸዋል::
- ተበዳሪው/ የንብረት ዋስትና ሰጭው በሐራጁ ቀንና ሰዓት ጨረታ በሚካሄድበት ቦታ መገኘት የሚችሉ ሲሆን በጨረታው ባይገኙም ግን ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል::
- ጨረታው የሚካሄደው ጎልደን ጌት ሆቴል አጠገብ በሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ. ደሴ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ውስጥ ለጨረታው በተዘጋጀው ቦታ ይሆናል::
- የጨረታው አሸናፊ(ገዥ) ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጭዎችን ይከፍላል::
- ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ቀሪ የሊዝ ክፍያ ዕዳ ደግሞ ወደ አሸናፊው/ገዥው የሚተላለፍ ይሆናል::
- የጨረታው አሸናፊ ንብረቱ በሚገኝበት የከተማ አስተዳደር ዘንድ ቀርቦ ባሸነፈበት ንብረት ላይ የሚከፈሉ ክፍያዎችን፣ግብር እና ታክስ እንዲሁም ለመንግስት የሚከፈል 15% (አስራ አምስት በመቶ) የተጨማሪ እሴት ታክስ ካለ ይከፍላል::
- በባንኩ የብድር ፖሊሲና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟሉ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢዎች ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል::
- ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት የሚቻል ሲሆን፣ለተጨማሪ መረጃ አበሲንያ ባንክ ደሴ ዲስትሪክት ህግ ክፍል በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይቻላል::
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት አለው::
- ማሳሰቢያ፤ በሰንጠረዡ ላይ ያለው የቦታ ስፋት በመንገድ መስፋፋት ምክንያት የተቀነሰውን የቦታ ስፋት ማለትም 104 ካ.ሜ ተቀንሶ የተቀመጠ መሆኑን እንገልፃለን፡
|
የተበዳሪው ስም |
ከተበዳሪው የሚፈለግባቸው ቀሪ ዕዳ |
የመያዣ ሰጭዎች ስም |
የመያዣ ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ |
የጨረታው መነሻ ዋጋ (በብር) |
ጨረታው የሚካሄድበት ቀንና ዓ.ም |
የምዝገባ ሰዓት |
ጨረታው የሚከናወንበት ሰዓት |
ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ |
የመያዣ ንብረቱ አገልግሎት |
የቦታው ስፋት (በካ ሜ) |
የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር |
|
አቶ አንዱዓለም ኃይሌ መክብብ |
እስከ ጥር 15 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ ብቻ ያለው ተሰልቶ ብር 11,880,355.36 |
አቶ አንዱዓለም ኃይሌ መክብብ |
አማራ ክልል፣ ኮምቦልቻ ሪጅዮ ፖሊታን ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 04 |
14,843,334.18 |
የካቲት 19 ቀን 2018 ዓ.ም |
3:30- 4:30 |
4:30-5:30 |
አቢሲንያ ባንክ አ.ማ ደሴ ዲስትሪክት ጽ/ቤት |
ለኢንዱስትሪ/ ማኑፋክቸሪንግ |
1896 |
7091/ ሊዝ/ኮ/ቲ አገ/ቀ04 |