Your cart is currently empty!
የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር መሬት መምሪያ ለመኖሪያ አገልግሎት 130 እና የንግድ 10 ቦታዎች በድምሩ 140 ቦታዎችን በጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል
Addis Zemen(Jan 26, 2026)
የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር መሬት መምሪያ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዘ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት በ2008 በጀት ዓመት 2ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ለመኖሪያ አገልግሎት 130 እና የንግድ 10 ቦታዎች በድምሩ 140 ቦታዎችን በጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል።
በመሆኑም፡-
መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ/ድርጅት/ ይህ ማስታወቂያ በአማራ ቴሌቪዥን ጨረታው እንደሚጀምር ከተነገረበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ የሥራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ : ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል ቀበሌ 08 ከአዲሱ መሬት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 310 በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላል። የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 11፡00 ሰዓት ብቻ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በቢሮ ቁጥር 310 ይሆናል።
ጨረታው የሚዘጋው በ10ኛው ቀን ከቀኑ በ11፡00 ሰዓት ይሆናል።
ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ጀምሮ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሲሆን ጨረታ የሚከፈትበትን ቦታ በተመለከተ በውስጥ ማስታወቂያ የሚገለጽ ይሆናል።
ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በመምሪያው የውስጥ ማስታወቂያ – መለጠፊያ ሰሌዳ እና በBahirdar City Communication የፌስ ቡክ ገፅ ማግኘት ይቻላል።
መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር መሬት መምሪያ
(ባሕር ዳር)