የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ


Be’kur(Jan 26, 2026)

የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ጎንደር ዞን በፋርጣ ወረዳ የጋሳይ መሪ ማዘጋጃ ቤት የከተማ ቦታን ስለመያዝ በሚደነግገዉ አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ንኡስ 1 መስረት በ2018 በጀት አመት 1ኛ ዙር ጨረታ ለመኖሪያ አገልግሎት 5 ቦታዎችን ለድርጅት አገልግሎት 5 ቦታዎችን በድምሩ 10 ቦታዎችን በጨረታ ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡

  1. በጨረታዉ መሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛዉም ሰዉ ወይም ድርጅት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛትና መጫረት ይችላሉ፡፡
  2. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ቀን ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት በመንግስት የሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 በመሪ ማዘጋጃ ቤቱ ዉስጥ ይሆናል፡፡
  3. ጨረታዉ የሚዘጋዉ በ10ኛዉ ቀን ከቀኑ በ11፡00 ነው፡፡
  4. ጨረታዉ የሚከፈተዉ ማስታወቂያ በወጣ በ11ኛዉ ቀን ከጠዋቱ በ3፡00 በመንግስት የሥራ ሰዓት ይሆናል።
  5. ለበለጠ ዝርዝር መረጃ የጨረታ ማስታወቂያዉ ከሚለጠፍበት ቦታዎች ላይ ማየት የሚቻል ሲሆን በስልክ ቁጥር 058 253 01 26 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።

የጋሳይ መሪ ማዘጋጃ ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *