Your cart is currently empty!
አፋር አርብቶ አደር ልማት ማህበር (APDA) የ2025 G.C. የፋይናንስ ሂሳብ በውጭ ኦዲተር እንዲመርመር ይፈልጋል
Reporter(Jan 28, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
አፋር አርብቶ አደር ልማት ማህበር (APDA) በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ በሚፈቅደው መሠረት የድርጅቱን የ2025 G.C. የፋይናንስ ሂሳብ በውጭ ኦዲተር እንዲመርመር ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሁሉም ተጫራቾች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ከ28/1/2026 G.C. ከጧት 8፡00 AM እስከ 11/2/2026 G.C. ከሰዓት 4፡00 PM ድረስ (15 ተከታታይ ቀናት) በሰመራ ከተማ፣ አፋር ክልል በሚገኘው የድርጅቱ ዋና ቢሮ በአካል በመቅረብ የፋይናንስና የቴክኒክል ፕሮፖዛላቸውን በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይችላሉ።
የተጫራቾች መስፈርቶች:
ተጫራቾች ከሚከተሉት መስፈርቶች ሁሉንም ማሟላት ይኖርባቸዋል፦
- የ2026 G.C. የታደሰ የንግድ ፈቃድና 15% VAT ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ፎቶኮፒ፤
- የዘመኑን ግብር ከፍለው መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ፤
- ለሥራው የሚመደቡ ባለሙያ ሰራተኞች ዝርዝርና የትምህርት/ሙያ ዝግጅታቸው፤
- የኦዲት ሪፖርቱን በስንት ቀናት ውስጥ አጠናቅቀው እንደሚያቀርቡ ግልፅ መግለጫ፤
- የኦዲት ሪፖርቱን በIPSAS መመሪያ (Standard) መሠረት ማዘጋጀት የሚችሉ መሆን፤
- በጨረታው የሚሳተፉ ተመሰከረላቸው የሂሳብ ባለሙያዎችና ኦዲተሮች መሆን አለባቸው፡፡
የጨረታ መክፈቻ
ጨረታው በ12/2/2026 ዓ.ም ከጧት 10፡30 AM ሰዓት ጀምሮ በድርጅቱ ዋና ቢሮ፣ በሰመራ ከተማ፣ አፋር ክልል ውስጥ በተጫራቾች ወይም በህጋዊ ወኪሎቻቸው ተገኝተው ይከፈታል።
ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡ በስልክ ቁጥር፡ 0911787073 መደወል ይቻላል።