የደ/ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር ገልባጭ መኪኖችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል


Addis Zemen(Jan 31, 2026)

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የደ/ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለሚያመርተው ቬኒር እና ፓላይ ውድ ጣውላ ግብዓት የሚሆን የባህር ዛፍ ግንድ ጫካው ከሚገኝበት ከደ/ብርሃን ወደ ደሴ በሚወስደው መንገድ ከሚገኘው አባ ሞቴ ቀበሌ ልዩ ስሙ ወንበር አንባ አካባቢ ደን ሳይት እና ጉዶበረት ቀበሌ ዱቤ አገር ደን ሳይት የተቆረጠ ግንድ የሚያመላልሱ ገልባጭ መኪኖችን በዘርፉ የተሰማሩ ባለንብረቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ከሆነው ባለንብረት ጋር የኮንትራት ውል በመግባት ግንዱ ተጭኖ እስከሚያልቅ ድረስ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሰረት፦

  1. በዘርፉ የተሰማራና የንግድ ስራ ፈቃዱን ያሳደሰ እና ስድስት ወር ያላለፈው ጨረታ ለመሣተፍ የሚያበቃ የገቢዎች የጨረታ ከሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2.  የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር ያላቸው፡፡
  3.  የቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትና ሌሎች የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች ለሁለቱም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው::
  6. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው::
  7. በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ካለም አንድ ሰረዝ በማድረግ ፊርማቸውን ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
  8.  ድርጅቱ ከፍያ የሚፈፅመው በቢያጆ ስለሆነ ለመኪናው የሚያስፈልገውን ወጪ የነዳጅ እና ሌሎች ሁሉንም ወጪዎች የሚሸፍነው ባለመኪናው ይሆናል፣
  9. ተጫራቾች ኦሪጅናል የጨረታ ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይህ ውስን ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት የሚቆይ ስለሆነ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታውን ሰነድ ገቢ ማድረግ ይችላሉ፡፡
  10.  ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ በካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ ውስጥ በይፋ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ከመከፈት እይታገድም::
  11. የመፈቻ ቀኑ የህዝብ በዓል ወይም እሁድ ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  12. አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የሚሆን ገንዘብ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብር 300,000.00 /ሦስት መቶ ሺህ ብር) ማስያዝ አለበት፤
  13.  መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0910368437 ደውለው ይጠይቁ

የደ/ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር

ደብረ ብርሃን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *