የምሥራቅ ጎጃም ዞን አልማ ልማት ጽ/ቤት ኤሌክትሮኒክስ፣ የጽህፈት መሳሪያ እንዲሁም ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል


Be’kur(Feb 02, 2026)

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የምሥራቅ ጎጃም ዞን አልማ ልማት ጽ/ቤት

  • ሎት 1 ኤሌክትሮኒክስ፣
  • ሎት 2 የጽህፈት መሳሪያ እንዲሁም
  • ሎት 3 ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል፡፡ 

ስለዚህ በዘርፉ ፈቃድ ያላችሁ እና በጨረታዉ መሳተፍ የምትፈልጉ እንዲሁም መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3.  ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4.  ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ደብረ ማርቆስ በሚገኘው ምስ/ጎጃም ዞን አልማ ልማት ጽ/ቤት አብማ መስመር ዶ/ር ይልቃል ዓይን ህክምና ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  5.  ተጫራቾች የጨረታ ማስከቢሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሚወዳደሩበት የሥራውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዉስጥ የጨረታ ሰነዱን ሞልተዉ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  7. ጨረታው በ7ኛው ቀን 11፡00 ላይ ይታሸጋል፡፡ በ8ተኛው ቀን 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  8. ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ምሥራቅ ጐጃም ዞን አልማ ልማት ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 771 34 05 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የምሥራቅ ጎጃም ዞን አልማ ልማት ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *