የወልድያ ከተማ አስተዳደርር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በ2018 በጀት አመት መደበኛ በጀት ለሚያሰራው የመሰረተ ልማት የግንባታ ስራዎች፣ የውሃ ተፋሰስ ግንባታ ስራ፣ የካልቨረት ግንባታ ስራ፣ የጠጠር መንገድ ጥገና ስራ እና የእቃ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራትና መግዛት ይፈልጋል


Be’kur(Feb 02, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የወልድያ ከተማ አስተዳደርር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በ2018 በጀት አመት መደበኛ በጀት ለሚያሰራው የመሰረተ ልማት የግንባታ ስራዎች፣የውሃ ተፋሰስ ግንባታ ስራ፣ የካልቨረት ግንባታ ስራ ፣ የጠጠር መንገድ ጥገና ስራ እና የእቃ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራትና መግዛት ይፈልጋል ፡፡

ስለዚህ በጫረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ሁሉ ለግንባታ ስራ የተለያ ደረጃ ባላቸው የስራ ተቋራጮች ና አቅራቢዎች ማሰራት እና  መግዛት ይፈልጋል፡፡

  • ሶስት ሳይት የውሃ ተፋሰስ ግንባታ ስራ በመደበኛ በጀት፤ የካልቨረት ግንባታ  ስራ በሎት በመደበኛ በጀት፡፡ ሁለት ሳይት የጠጠር መንገድ ጥገና ስራ በመደበኛ በጀት፡፡ ሎት 1. ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ በመደበኛ በጀት ፤ሎት 2. የጽህፈት መሳሪያ ግዥ በመደበኛ በጀት፡፡ ሎት3. የቆሻሻ ገንዳ በመደበኛ በጀት የተለያዩ ደረጃዎች ባላቸው የስራ ተቋራጮችና አቅራቢዎች አስፈላጊ የሆኑትን የግንባታ ማቴሪያሎትና የእጅ ዋጋ ችለው ለሚሰሩ ተወዳዳሪዎችና የእቃ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተቋራጮችና አቅራቢዎች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

1. ታደሰ ንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ  የሚችሉ፡፡

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(ቲን ነበር) ያላቸው፡፡

3. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡

4. ማንኛውም የስራ ተቋራጭ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡

5.  ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የጠቅላላ ዋጋ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ  ወይም በመ/ቤታችን ገንዘብ ያዥ/ ገቢ ሆኖ ገቢ የተደረገበትን ደረሰኝ ኮፒ አድርጎ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ለውሃ ተፋሰስ ግንባታ ግንባታ ስራ ለያንዳደቸው  ብር 30,000.00፡፡ ለካልቨረት ግንባታ  ስራ  ብር 9,000፡፡ ለጠጠር መንገድ ጥገና ስራ ለያንዳደቸው 30,000፡፡ ሎት 1. ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ ብር 10,000.00 ሎት 2. የጽህፈት መሳሪያ ግዥ  ብር 6,000.00 ፤ሎት 3 የቆሻሻ ገንዳ  ግዥ ብር 40,000

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ወልዲያ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር  በመምጣት ለእያንዳንዳቸው ግንባታዎችና ዕቃ ግዥዎች የማይመለስ ብር ብር 200  መግዛት ይችላሉ፡፡

7. ማንኛውም ተጫራች ሰነድ ገዝቶ መጫረት የሚችሉትው የመረጡትን የግንባታ ስራ 3 ሳይት ብቻ መርጦ መግዛትና መወዳደር ይችላል፡፡ ከዚህ ውጭ ወይም ከተፈቀደው ሰነድ በላይ ገዝቶ የተገኘ ተጫራች ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡ ለአዲስ ግንባታ ስራ ተወዳዳሪዎች አሸናፊ ከሆኑ የማቴሪያል ቴስት ማቅረብ አለባችሁ፡፡

8. ማንኛውም የግዥ ወይም የግንባታ ስራዎች የጨረታ ሰነዱን ዋጋ   መሙሊያ ላይ ምንም አይነት ነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የጠፋ የማይነበብ ተደጋግሞ የተጻፈ እንዲሁም የማይነበብ የማስረጃ  ፎቶ  ኮፒ አያይዞ የቀረቡ ተወዳዳሪዎች ከጨረታ ውጭ ይሆናሉ፡፡

9. የጨረታ ሰነዱን በኦርጅናልና በኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግ የሚወዳደሩበትን ሳይት ወይንም እቃ በፖስታው ላይ በመጻፍና  በማዘጋጀት የድርጅቱን ማህተምና ፈርማ ሙሉ አድራሻ በመግለጽ በተለያየ ፓሰታ አሽጎ ወልድያ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳር ቡድን  በመምጣት በተዘጋጅው የጨረታ ሳጥን  ማሰገባት ይኖርባቸዋል፡፡

10.  በጨረታ አሸናፊ ከሆኑ ለተወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 10በመቶ የውል ማስከበሪያ ማሰያዝ ይኖርባችኋል፡፡

11.  በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ማህበራት ከሆኑ ካደራጃቸው አካል የድጋፍ ደብዳቤና የመልካም ስራ አፈጻጸም ወቅታዊ የሆነ መረጃ በሃላፊ የተፈረመ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡

12.  ጨረታው ተግባራዊ የሚሆነው መመሪያ ቁጥር 1/2003 እና በ2014 ግንቦት ወር ላይ ተሻሽሎ የወጣውን አዲሱን የግዥ መመሪያ ተግባራዊ የሚያደርግ ይሆናል፡፡

13.  የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ ማስረጃ ወይም መረጃ ተቀባይነት የለውም፡፡

14. ተጫራቾች የተሳሳተ መረጃ ወይም ማስረጃ ማቅረብ በህግ ያስቀጣል ከጨረታውም ውድቅ ይደረጋል፡፡

15. ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 13 ለተዘረዘሩት መስፈርቶች  ለሁሉም ተጫራቾች (ተወዳዳሪዎች) ገዥ ይሆናል፡፡

1. የውሃ ተፋሰስ ግንባታ ስራ በመደበኛ በጀት 

የውሃ ተፋሰስ ግንባታ ስራ የወልድያ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በ2018 በጀት አመት በመደበኛ በጀት ለሚያሰራው የውሃተፋሰስ ግንባታ ስራ ከሸዋየ ቤት እሰከ ሁሴን ኑረየ ቤት 0.1ኪ/ሜ ኮድ woldia–CW-DR-cip–06—01-2025/2026 ፣ከሁሴን ኑረየ ቤት እሰከ ዘምዘም ሙሃመድ ቤት 0.1 ኪ/ሜ ኮድ woldia–CW-DR-cip–06—02-2025/2026 እና፣ ከዘምዘም ሙሃመድ ቤት እሰከ ሀሴት ት/ቤት 0.15ኪ/ሜ ኮድ woldia–CW-DR-cip–06—03-2025/202 በደረጃ 7 እና በላይ ሙያ ባላቸው የስራ ተቋራጮች አወዳድሮ  ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ለውሃተፋሰስ ግንባታ ስራ የሚያስፈልጉ ማንኛውንም የግንባታ ማቴሪያሎችና የእጅ ዋጋችሎ ወይም አቅርቦ ለመስራት ለሚፈልጉ ሁሉ በተዘጋጀው ፕላንና የሰራ ዝርዝር እና  ዲዛይን መሰረት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን 25/05/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 25/06/2018 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሰራ ሰዓት በመምጣት መውሰድ ይቻላል፡፡ የጨረታ ሰነዱን ወልድያ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳር ቡድን በመምጣት  በተዘጋጅው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማሰገባት አለበት፡፡ የጨረታ ሳጥኑም በዚሁ ቀን 25/06/2018 ዓ.ም ከጧዋቱ 4፡00 ታሽጎ ከጧዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ  ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል፡፡

የጠጠር መንገድ ጥገና ስራ እና ካልቨረት ግንባታ ስራ ከደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ 

የወልዲያ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በ2018 በጀት አመት በመደበኛ በጀት ለሚያሠራው የጠጠር መንገድ ጥገና ስራ ሴቭ ዘችልድረን እሰከ መምህራን ኮሌጅ 0.55 ኪ/ሜ ኮድ woldia-—GM—cip–03-02-2025/2026፣ የጠጠር መንገድ ጥገና ስራ የጁገነት ቀበሌ አደንጉር ሙሉ መነፈሻ ቤት ፊት ለፊትት 0.25ኪ/ሜ ኮድ woldia-GM-cip–03-01-2025/2026 እና ካልቨረት ግንባታ ስራ አራት ሳይት በሎት1. ኮድ  woldia – CW-CIP-CL–05-01-2025/2026፣ የግንባታ ስራ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ከየካቲት 25/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 26/06/2018 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሰራ ሰአት በመምጣት መውሰድ ይቻላሉ፡፡ የጨረታ ሰነዱን ወልድያ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን በመምጣት በተዘጋጅው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በቀን 26/06/2018 ዓ.ም ከጧዋቱ 4፡00  ድረስ ማሰገባት አለበዎት፡፡ የጨረታ ሳጥኑም በዚሁ ቀን 26/06/2018 ዓ.ም ከጧዋቱ 4፡00 ታሽጎ ከጧዋቱ 4፡30 ተጫራቾች  ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል፡፡

2.  የእቃ ግዥ በመደበኛ በጀት

የወልድያ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በመደበኛ በጀት በ2018 ዓ/ም የተለያዩ ሎት ያላቸው እቃዎችን  በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሎት 1. የኤሌክትሮኒክስ  ኮድ woldia–CW- cip -ICT-01—01–2025/2026 ሎት 2. የጽ/መሳሪያ ኮድ woldia– CW cip -ST-02—01–2025/2026፤  ሎት 3. የቆሻሻ ገንዳ፡፡

ስለዚህ የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከየካቲት 25/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ የካቲት 16/2018 ዓ/ም ዘወትር በስራ ሰዓት በመምጣት መውሰድ ይቻላል፡፡ የጨረታ ሰነዱን ወልድያ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳር ቡድን በመምጣት የጨረታ ፖስታውን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በቀን 16/06/2018 ዓ/ም ከጧቱ 4፡00ማስገባት አለበዎት የጨረታ ሳጥኑም የካቲት 16/2018 ዓ/ም ከጧቱ 4፡00 የጨረታ ሳጥኑታሽጎ ከጧቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል፡፡ በጨረታ አሸናፊ ከሆኑ ያሸነፉበትን ንብረት በራስዎ ወጭ አጓጉዘው ወልድያ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ንብረት ክፍል ገቢ ያደረጋሉ፣ ካሸነፉት ንብረት ውስጥ ትክክለኛውን እቃ ካላቀረቡ በራስዎ ወጭ መልሰው ትክክለኛውን እቃ ያቀርባሉ፡፡ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ሁሉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ  በአካል በመገኘት ወይንም በስልክ ቁጥር 03 33 31 13 31 በመደወል መረጃ ማገኘት ይቻላል፡፡መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ  ጨረታው የመከፈቻ ቀኖች ከላይ በተገለጹት ሲሆን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡                                                          

የወልድያ ከተ/አስ/ ከተ/ መሰ/ ል/ መምሪያ