Your cart is currently empty!
የተለያዩ ጌጣጌጥና የልደት ዲኮር እንዲሁም የ2 ዲስፕሌይ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Addis Zemen(Feb 05, 2026)
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት ፅዮን ሀይሌ እና የፍ/ባለዕዳ እየሩሳሌም ሙሉጌታ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ/04427 በ6/02/2017 ዓ/ም በኮ/መ/ቁ/ 08087 ሚያዚያ 9 ቀን 2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ፍርድ ለማስፈጸም በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 02 የማነ እና ተ/ጽዮን ጄኔራል ትሬዲንግ ሕንፃ ውስጥ የሚገኝ የተለያዩ ጌጣጌጥና የልደት ዲኮር እንዲሁም 2 ዲስፕሌይ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 76,170 (ሰባ ስድስት ሺህ አንድ መቶ ሰባ ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ የካቲት 18 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 5፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሦስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በሕጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት