Your cart is currently empty!
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በሀዲያ ዞን የምሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽህፈት ቤት የተለያዩ ግንባታዎች ለማሰራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 06, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በሀዲያ ዞን የምሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ሎት1 በምሻ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ስር በአሽዋላ ዋቼ ጤና ጣቢያ ላይ የሚሰሩ ግንባታዎች
1ኛ አድስ የአመድ መጣያ ጎድጎድ ማስቆፈርና ማስገንባት/Construction of New Ash Pit
2ኛ አዲስ የእንግዴ ልጅ መጣያ ጉድጓድ ማስቆፈርና ማስገንባት/Construction of Placenta Pit
3ኛ አዲስ የመርፌና ስርንጅ ማቃጠያ ግንባታ /Construction of new lncinerator
4ኛ Construction of Fanced New Solid Waste disposal
5ኛ አዲስ የልብስ ማጠቢያ ማስገንባት/Construction of New Cloth Wasing Besin
ሎት2 በምሻ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ስር በሚገኙ
1ኛ በደንጋውራ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ክፍል/MHM Construction
2ኛ በሽሮ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ክፍል/ MHM Construction
3ኛ በሽሮ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የሴቶች ሽንት ቤት ግንባታ /Dry Girls Latrine For Four Seats ላይ የተለያዩ አይነት የግንባታ ስራዎችን በዲዛይኑ መሰረት ለማሰራት በዘርፉ የተደራጁ ማህበራትን ወይም የግል ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት ተወዳዳሪ ተጫራቾች፡-
1ኛ. በመስኩ የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው
2ኛ የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት ያላቸው
3ኛ. የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ያላቸው
4ኛ. የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው
5ኛ. የመልካም ስራ አፈጻጸም ሰርተፍኬት ያላቸው
6ኛ. የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ያላቸው
7ኛ. የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ያላቸው ድርጅቶች በሀዲያ ዞን የምሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ከግዥ ፋ/ን/አስ/ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 16 በአካል በመምጣት የተዘጋጀውን የግንባታ ጨረታ ሰነድ ጋዜጣው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ግንባታ ሎቶች በተናጠል ብር 400 (አራት መቶ ብር) የማይመለስ ብር በመክፈል ዘውትር በስራ ሰዓት ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
8ኛ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎቶች ብር 10000 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ሰነድ በቴክኒካል ጨረታዎች ጋር አሽጎ ማቅረብ አለባቸው፡፡
9ኛ. ማንም ተጫራች የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ መጨረሻ ላይ ዋጋውን በግልጽ በአሃዝና በፊደል መጻፍ አለባቸው:: ያልተጻፈው ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
10ኛ. የጨረታውን መወዳደሪያ ዋጋ ጽ/ቤቱ ባዘጋጀው ፎርማት ላይ ብቻ መሙላት አለባቸው፡፡
11ኛ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በ16 (በአስራ ስድስተኛው ቀን) ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በ5፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የበዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በቀጣይ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
12ኛ ተወዳዳሪ ተጫራቾች የመወዳሪያ ፖስታዎችን ቴክኒካል አንድ ኦርጅናል ሁለት ኮፒ ሰነዶችን እና የጨረታ ማስከበሪያ ወይም በሁኔታ ያልተመሰረታ የጨረታ ማስከበሪያ እያንዳንዱን በማሸግ አራቱንም በአንድ ፖስታ በማድረግ ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናል ሁለት ኮፒ ሰነድ ሦስቱንም በአንድ ፖስታ በማድረግ እና ቴክኒካልና ፋይናንሻል በአንድ እናት ፖስታ በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
13ኛ ጨረታው የቴክኒክ መስፈርቱን ካሟሉት አቅራቢዎች መካከል ዝቅተኛ ዋጋ ላቀረበው ተጫራች አሸናፊ ይደረጋል።
14ኛ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0910 452 656/0916 673 483 ደውሎ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን።
ማሳሰቢያ ለግንባታ ስራ ያለው ጊዜ አጭር ከመሆኑ አንፃር አንድ ተጫራች ከአንድ ጨረታ በላይ መጫረትም ሆነ የጨረታ ሰነድ መግዛት አይችልም፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በሀዲያ ዞን የምሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት