በየካ/ክ/ከ ወረዳ 02 አስተዳደር የፋ/ጽ/ቤት ለ2018 በጀት አመት በመጀመሪያ ዙር ያልቀረቡ የተለያዩ እቃዎች እና አገልግሎቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት/አገልግሎቱን ማግኘት ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 07, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

በየካ/ክ/ከ ወረዳ 02 አስተዳደር የፋ/ጽ/ቤት ለ2018 በጀት አመት በመጀመሪያ ዙር ያልቀረቡ አላቂ የቢሮ ዕቃ(እስቴሽነሪ)፣የደንብ ልብስ፣የፅዳት እቃ ፣የጥገና(የአይቲ) አገልግሎት፣የሰራተኞች ካፊ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት/አገልግሎቱን ማግኘት ይፈልጋል፡፡ 

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የምትችሉ ነጋዴዎች መወዳደር ትችላላቹህ፡፡

  • የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  • የእሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናችሁን የሚገልፅ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  • በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  • በሚሰጠው አገልግሎት ከመ/ቤቱ ጋር ውል ወስዶ በሚፈለገው ሰአት ማቅረብ እና
  • አገልግሎቱን መስጠት የሚችል፡፡
  • የሚያስገቡትን ሰነድ ማህተም ማድረግ፣መፈረም እና አለመሰረዝ፡፡
  • ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀን የካ ክፍለ ከተማ | ወረዳ 2 ፋ|| ቤት የጨረታ መመሪያ፣የዕቃና አገልግሎት እስፔስፍኬሽን አጠቃሎ የያዘ የጨረታ ሰነድ በአካል መጥተው በማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) ብቻ ገዝተው መውሰድ ይችላሉ፡፡
  • አሸናፊ በሚሆኑበት እቃ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ ማስያዝ የሚችል፡፡
  • ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10(አስር) ተከታተይ የስራ ቀን በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን በ3፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት የሚከፈት ሲሆን የሚከፈትበት ቀን እሁድ ቅዳሜ / የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡

የጨረታ ማስከበሪያ በተመለከተ

  • ደንብ ልብስ 10,000(አስርሺህ) 
  • እስቴሽነሪ  5,000.00(አምስትሺህ)፣
  • የጽዳትእቃ 10,000.00(አስርሺህ)፣
  • ትራንስፖርት 5,000(አምስት ሺህ)፣
  • ጥገና አገልግሎት 3,000.00(ሶስት ሺህ)እና
  • የሰራተኞች ካፌ አገልግሎት 5,000.00 (አምስት ሺህ) CPO ብቻ ማስያዝ እንዳለባቸው እየገለፅን በድጋፍ ደብዳቤ ለምታመጡ ነጋዴዎች የምታስገቡት እቃ በሃገር ውስጥ ለሚመረት እቃዎች፣ለትራንስፖርት፣ለካፌ አገልግሎትና ለጥገና አገልግሎት የሚናስተናገድ ሲሆን ከሀገር ውጪ ለሚመረቱ/ለሚገቡ ምርቶች በድጋፍ ደብዳቤ የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ለሚያቀርቡት እቃ ናሙና ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ግድ ነው፡፡

የሚያስገቡትን የቴክኒክ እና ፋይናሺያል ሰነድ ዋና እና ኮፒ ለየብቻ በፖስታ ታሸጎ መግባት አለበት፡፡

መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ ፡- ፈረንሳይ አደባባይ ፊትለፊት 100 ሜትር ገባ ብሎ የካ ክ/ከ ወረዳ 02 አስተዳደር ፋ/ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 9
መረጃ በስልክ ቁጥር 0111 54 89 03 መደወል ይችላሉ፡፡

በየካ/ክ/ከ ወረዳ 02 አስተዳደር የፋ/ጽ/ቤት