በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የመርካቶ ቁጥር 2 መ/ግ/ከ/ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ አላቂ እና ቋሚ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 07, 2026)

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 003/2018

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የመርካቶ ቁጥር 2 ///ቅርንጫፍ /ቤት 2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ አላቂ እና ቋሚ እቃዎች ማለትም ሎት 1 የተለያዩ የደንብ ልብስ፣ ሎት 2 የተለያዩ አላቂ የፅሕፈት መሣሪያዎች፣ ሎት 3 የሕትመት ውጤቶች፣ ሎት 4 የተለያዩ አላቂ የፅዳት እቃዎች፣ ሎት 5 የተለያዩ ቋሚ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ሎት 6 የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣ ሎት 7 የተለያዩ ለቢሮ እቃዎች ለጥገና አገልግሎት የሚውሉ እና አልሙኒዬም የጥገና መለዋወጫ እቃዎች፣ ሎት 8 ቋሚ የአይቲ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 9 የተለያዩ የቢሮ ቋሚ እቃ እና የአዳራሽ መጋረጃ፣ ሎት 10 የቢሮ ምንጣፍ ማጠብ፣ ሎት 11 የታሸገ ንፁሕ የመጠጥ ውሃ፣ ሎት 12 የተለያዩ ለላይብረሪ የሚያገለግሉ መጽሐፍቶች እና ሎት 13 በመ/ቤታችን የሠራተኞች ክበብ የምግብ እና ትኩስ መጠጥ የሚያቀርብ እንዲሁም የካፌ አገልግሎት የሚሰጥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሕጋዊ መስፈርቶች አሟልታችሁ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

1. የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ የሚያስችል ደብዳቤ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ሠርተፍኬት እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

2. ተጫራቾች ለጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400/አራት መቶ ብር/ በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን ሙሉ ቀን ጨምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ልደታ መናፈሻ ፊት ለፊት በላይ ተክሉ ኬክ ቤት ጎን በሚገኘው ዊዝ ደም የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማኅበር መርካቶ .2 /////ቤት ሕንፃ ላይ 7ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 704/705 የግዥ አገልግሎት ቡድን በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን በጥሬ ገንዘብ መግዛት ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከሎት 1 እስከ ሎት 12 ያለውን ብር 7,000.00 (ሰባት ብር) እና ለሠራተኛ ክበብ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ .. (C.PO.) ብቻ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ መርካቶ ቁጥር 2 /////ቤት (Addis Ababa City Government Revenues Bureau Merkato No 2 Medium Tax Payers Branch Office) በሚል ስም በማሠራት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

4. የጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች ለሆኑት ከአደራጅ መሥሪያ ቤት የጨረታ መወዳደሪያ ዋስትና ደብዳቤ በሚመለከተው የሥራ ኃላፊ የተረጋገጠ ደብዳቤ ማጻፍ እና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

5. ዋጋ ያልተሞላበት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ ከሎት 1 እስከ ሎት 12 ያሉትን የምትወዳደሩበትን እቃዎችንአገልግሎቶች ብቻ በመለየት የዋጋ ማወዳደሪያ ሰንጠረዥ ላይ በመክበብ ወይም ምልክት ማድረግ እና ሎት 13 የሠራተኞችን ካፌ በተመለከተ የሚቀርቡ ዝርዝር አገልግሎቶችን በደንብ በማንበብ እና በመረዳት አገልግሎቶችን ለማቅረብ ፍቃደኛ መሆንዎትን በፊርማ በማረጋገጥ ሰነዱን ኦርጂናሉን እና ኮፒ (ዋናውንና ቅጂውን) ከቴክኒክ ሰነዶች ጋር አብሮ መያያዝ አለበት ፡፡

6. የፋይናንሻል ወይም የዋጋ ማወዳደሪያ ሰንጠረዥ ዋጋው ከነቫቱ ተሞልቶ ብቻውን በኦርጅናል እና ኮፒ (ዋናውና ቅጅ) ለየብቻው ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡

7. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሠነድ በድምሩ በአራት ኤንቨሎኘ ኦርጂናልና ኮፒውን ወይም (ዋናውንና ቅጂውን) ለየብቻ በሠም ወይም በሌላ ማጣበቂያ በማሸግ በመ/ቤታችን በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ የጨረታ ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን እስከ 10ኛው የሥራ ቀን ቅዳሜን ጨምሮ እስከ ጠዋቱ 400 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

8. ተጫራቾች በተሳተፉበት አገልግሎቶች ወይም በሚወዳደሩበት መስክ ላይ ለመ/ቤቱ ኮሚቴዎች ሳምፕል ማቅረብ ማለትም የደንብ ልብስ፤ የፅህፈት መሣሪያዎች፣ የሕትመት ውጤቶች፣ የፅዳት እቃዎች፣ ለጥገና የሚውሉ እቃዎች፣ የመኪና እቃዎች፣ የውሃ ናሙና እና ናሙና ለተጠየቀባቸው ፍላጎቶች ለሁሉም ሳምፕል ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ እንዲሁም በቀላሉ ለማንቀሳቀስ የማይችሉ ልዩ ልዩ ቋሚ እቃዎች ናሙና ለመሥሪያ ቤታችን ኮሚቴዎች በተጫራቾች ድርጅት ውስጥ በአካል ለማሳየት ፍቃደኛ መሆን ይጠበቅበታል፡፡ በተጨማሪም የሥራ ልምድ እና የመልካም አፈጻጸም ማስረጃ ለሚያስፈልጋቸው የሥራ ልምድና የመልካም አፈጻጸም ማስረጃዎችን ኮፒ አድርጎ ለማያያዝ ፍቃደኛ መሆን ይጠበቅበታል፡፡

9. የጨረታ ሣጥኑ ጨረታው በወጣበት 10ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 430 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤታችን የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ጨረታ የሚከፈትበት ቀን ዓመት በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን 430 ይከፈታል፡፡

10. አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡

11. ቅርንጫፍ /ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

12. የጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

13. እኩል ውጤት ያገኙ ተጫራቾች ተጨማሪ የማወዳደሪያ ሃሳብ እንዲያቀርቡ ይደረጋል:: ለሦስተኛ ጊዜ እኩል ከሆኑ በዕጣ እንዲለዩ ይደረጋል፡፡

14. የጨረታ መገምገሚያ ዘዴዎች በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በክፍል ሦስት እና በክፍል ስድስት በተጠቀሱት መሠረት ብቻ ይሆናል፡፡

15. ተጫራቾች ሁሉንም የመወዳደሪያ ሰነዶች ሕጋዊ ሥልጣን ባለው አካል ተፈርሞባቸውና የድርጅታቸውን ማሕተም አርፎባቸው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

16. የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ 60 ቀን እና ለተጨማሪ 28 ቀን በድምሩ 88 ቀን የሚቆይ ይሆናል፡፡

17. መሥሪያ ቤታችን ከአሸናፊ ድርጅቶች ጋር በጨረታ ሰነዱ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ ምንም የዋጋ ልዩነት ሳይኖር እስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡

ለበለ መረጃ፡በስልክ ቁጥር 0112 734 837 / 0112 732 771 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የመርካቶ ቁጥር 2 ///ቅርንጫፍ /ቤት