Your cart is currently empty!
በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ትምህርት ጽ/ቤት የህዝባዊ ሰራዊት ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 08, 2026)
በድጋሚ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ትምህርት ጽ/ቤት የህዝባዊ ሰራዊት ቅድመ አንደኛ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- የሰራተኞች ደንብ ልብስ
- አላቂ የቢሮ እና የትምህርት እቃዎች
- የህክምና እቃዎች
- ቋሚ የቢሮ እቃዎች
- የላብራቶሪ እቃዎች
ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርት የምታሟሉ ሁሉ በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ።
1. በመስኩ አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
2. የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተመዘገቡበት ማስረጃ ማቅረብ አለበት።
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት መረጃ ያላቸው።
4. ጥራት ያለው ዕቃ ማቅረብ የሚችሉና ጨረታ ከመከፈቱ በፊት የዕቃዎቹን ናሙና በፎቶ አስቀድሞ ማቅረብ የሚችሉ።
5. የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ ብር 10,000.00 /አስር ሺ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ /CPO/ ማስያዝ የሚችሉ።
6. ለጨረታ ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ ብር 200.00/ ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከግዢ እና ፋይናንስ ክፍል መግዛት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ የድርጅቱ ስም ከብ ማህተም እና ፊርማ በታሸገ ኢንቭሎፕ ዉስጥ በማድረግ ማስገባት አለባቸው።
8. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት በገዙት ዝርዝር ሰነድ ላይ በግልፅ መፃፍ አለባቸው ስርዝ ድልዝ ካለ ተጫራቹ ፊርማውን ከአጠገቡ ማሰቀመጥ ግዴታ አለበት።
9. ጨረታው ለአስር ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ11 ቀን ከቀኑ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ ወዲያውኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት በምክትል ርዕሰ መምህር ቢሮ ይከፈታል።
10.ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ የአንዱን ዋጋ የሞላውን በጠቅላላ ድምር ላይ ማሰቀመጥ ይጠበቅበታል።
11. ተጫራቹ የሸነፈበትን የጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ የተረጋገጠ ቼክ /CPO/ ማስያዝ ይጠበቅበታል።
12. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ፈረንሳይ ለጋሲዮን ከታክሲ ማዞሪያ ከፍ ብሎ የካ ኢንዱስትሪያ ኮሌጅ ፊት ለፊት የሚገኝው ህዝባዊ ሰራዊት ቅድመ አንደኛ አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
ስ.ቁ 011 114 0080 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል። P.O box 20055
በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ትምህርት ጽ/ቤት
የህዝባዊ ሰራዊት ቅድመ አንደኛ አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት