Your cart is currently empty!
የሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም ለህግ ታራሚዎች አገልግሎት የሚውል ማጣፈጫ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 08, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም ለህግ ታራሚዎች አገልግሎት የሚውል በማጣፈጫ በዘርፉ ከተሠማሩ ነጋዴዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ነጋዴዎች መወዳደር ይችላሉ፡-
- በዚህ ዘርፍ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑ ግብር የከፈሉ፣ ተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸውና የንግድ ምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን ማጣፈጫ ለ6 ወራት የሚፈለገው መጠን ጥራትንና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በየወሩ እስከ ተቋሙ ቅጥር ግቢ ድረስ አምጥተው ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በተራ ቁጥር 1 የተገለፁትን ህጋዊ ማስረጃዎች ለጨረታው ከሚቀርበው ዋጋ ጋር ዋናውንና ኮፒውን አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበርያ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ በባንክ በተረጋገጠ CPO 50,000 (ሃምሳ ሺህ) ብር ከዋናው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በሰነድ ላይ በተገለፀው አድራሻ በተከታታይ 15 ቀናት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ሳጥን የሚታሸገው በአስራ አምስተኛ ቀን በ4፡00 ሰዓት ሲሆን የጨረታ ሳጥን የሚከፈተው በዕለቱ ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ይከፈታል ይህ ቀን የበዓልም፣ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የማጣፈጫ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ አንድ ቀን ቀደም አድርጎ በማስገባት ጥራቱን ለጨረታ ኮሚቴ ማሳዬት አለበት፡፡
- ተጫራቾች ከሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም ግ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/ሥ/ሂደት ቀርበው ዝርዝር ሰነዱን 200 (ሁለት መቶ) ብር በማይመለስ በመክፈል መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ መረጃ ፡- በስልክ ቁጥር ፡-046-122-80 84 መደወል ይችላሉ :
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሀዋሳ
ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም