Your cart is currently empty!
ቦሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የደንብ ልብስ ግዥ፣ ለአላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ለህትመት፣ ለአላቂ የት/ት እቃዎች፣ አላቂ የጽዳት እና ሌሎች ዕቃዎች፣ ለተለያዩ አላቂ እቃዎችና አቅርቦቶች፣ ቋሚ የኤሊክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ እና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 08, 2026)
2ኛ ዙር ግልጽ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 የቦሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለቢሮና ለትምህርት አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች
- የደንብ ልብስ ግዥ
- ለአላቂ የቢሮ እቃዎች
- ለህትመት
- ለአላቂ የት/ት እቃዎች
- አላቂ የጽዳት እና ሌሎች ዕቃዎች
- ለተለያዩ አላቂ እቃዎችና አቅርቦቶች
- ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ
- ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሰለሆነም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳደሪዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውን ዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የሚያቀርብ።
- የገቢዎችእና ጉምሩክ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ቫት/ የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- የአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር መያያዝ የሚችሉ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 100 ብር/ አንድ መቶ ብር/ በመከፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ቦሪ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታ ማሰከበሪያ ለሁሉም ሎቶች 20,000 ብር (ሃያ ሺብር) በባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ አለበት።
- የመወዳደሪያ ዋጋው ከነቫት በማስቀመጥ በግልጽ ተጠቅሶ መጻፍ ይኖርበታል።
- የጨረታው ተሳታፊዎች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ ፋይናንሺያል እና ቴክኒካል ዋናውንና ኮፒ በፖስታ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡ ፡ በተጨማሪም የሚወዳደሩበት ዕቃ ናሙና /specification/ ማቅረብ አለባቸው።
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከታወቀ በኃላ በ15 ቀናት ውስጥ ከት/ቤቱ ጋር ውል መዋዋል አለበት።
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ደረጃውን የጠበቀ ዕቃዎችን ትዕዛዙ በደረሳቸው በአምስት የስራ ቀናት ውስጥ በናሙናው መሰረት አጠናቀው ለት ቤቱ ንብረት ክፍል ሲያስረክቡና በጥራት ኮሜቴ ተፈትሾ ሲያልፍና በተቋሙ ኃላፊ ገቢ እንዲሆን ከታዘዘ በኃላ ይከፍላቸዋል።
- የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ11ኛው የስራ ቀን ጠዋት 4፡00 የጨረታው ሳጥን ይታሸግና በዛው እለት በ4፡30 ሰዓት ቦሪ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋ/ግ/ንብ አሥ የቡድን መሪ ቢሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ሲታወቅ የውል ማስከበሪያ ካሸነፈበት ጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 10% በጥሬ ገንዘብ CPO በቅድሚያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ሁሉም ተጫራቾች ከ ጥር 1 ጀምሮ ገቢዎች እና ጉሙሩክ ባለስልጣን ባወጠው መመሪያ መሰረት ካሽ ሪጅሰተር ያለው ወይም QR ኮድ ያለው ደረሰኝ ማቅረብ አለባችው።
አድራሻ፡– ከአያት አደባባይ ወደ ጣፎ በሚወስደው መንገድ በግራ በኩል በመናፈሻ ፊትለፊት 300 ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል።
ለበለጠ መረጃ ፡– በስልክ ቁጥር ፡–
አስተዳደር ለሚኩራ ክ/ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ቦሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
cttx Advertising and Promotion cttx, cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Computer and Accessories cttx, cttx Education and Training cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Furniture and Furnishing cttx, cttx House Furniture cttx, cttx IT and Telecom cttx, cttx Materials cttx, cttx Office Furniture cttx, cttx Office Machines and Accessories cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Printed Advertising Materials cttx, cttx Printing and Publishing cttx, cttx Promotional Items cttx, cttx Shoes and Other Leather Products cttx, cttx Stationery cttx, cttx Textile, Electromechanical and Electronics cttx, Garment and Leather cttx, Garments and Uniforms cttx